am_tn/jer/08/20.md

1.8 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

ኤርምያስ ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

“እኛ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታል፡፡ “እኔ” እና “የእኔ” የሚሉት ቃላት ኤርምያስን ያመለክታሉ፡፡

መከሩ አልፎአል

“የመከር ጊዜ አልፎአል”

ነገር ግን እኛ አልዳንንም

ኤርምያስ የይሁዳ ሕዝብ የሚናገሩትን ያስተላልፋል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን እግዚአብሔር እኛን አላዳነንም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔም ተሰብሬአለሁ፣ ጠቁሬማለሁ፡፡ በእርስዋ ላይ በሆኑት አስከፊ ነገሮች እኔ አዝኛለሁ፤ እኔ ተስፋ ቆርጫለሁ

እነዚህ ዓረፍተ ሃሳቦች አጽንዖት ለመስጠት ከአንድ በላይ መንገድ በመጠቀም ተመሳሳይ ሃሳብ ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?

እነዚህ ጥያቄዎች የጠጠየቁት የይሁዳ ሕዝብ እንዳልዳኑ ዋናውን ነጥብ ለማስተላለፍ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በገለዓድ መድኃኒት አለ፣ በዚያ ሐኪሞች አሉ፣ ስለዚህ የውድ ሕዝቤ ፈውስ ለምን እንደማይከናወን ንገሩኝ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)