am_tn/jer/08/18.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስና እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ንግግር ያደርጋሉ፡፡

የእኔ ሃዘን አያልቅም

እዚህ ላይ “የእኔ” የሚለው ኤርምያስን ያመለክታል፡፡ የመጀመርያው የተጻፈበት ሃሳብ ግልጽ አይደለም ስለዚህ በዘመኑ ባሉት ትርጉሞች በተለያዩ መንገዶች ተተርጉሟል፡፡

አያልቅም

ይህ ቃል የኤርምያስን ጥልቅ ሃዘን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ግነት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም ታላቅ” ነው፡፡ (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ ትምሟል

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ኤርምያስን የሚወክል ሲሆን እርሱ የተሰማውን ነገርና ስሜቱን አጽንዖት የሚሰጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በጥልቅ የውስጥ ማንነቴ ሕመም ይሰማኛል” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

ይህ ከዚህ ቀጥሎ ለሚነገረው ነገር አንባቢው ትኩረት እንዲሰጥ የሚያነቃ ነው፡፡ “ትኩረት ስጥ”

የሕዝቤ ሴት ልጅ

ኤርምያስ ለሴት ልጅ የሚገባውን ዓይነት ፍቅሩን ለይሁዳ ሕዝብ በሚያሳይበት መንገድ ስለ እነርሱ ይናገራል፡፡ ይህንን በኤርምያስ 4፡11 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ውድ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሩቅ አገር

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ከግዞት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከግዞት ከሩቅ አገር” ወይም 2) ከይሁዳ ምድር በሙሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድራችን ዙርያ ሁሉ”

እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉስዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን?

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ የይሁዳ ሕዝብ እግዚአብ|ሔር ለምን እነርሱን እንዳላዳናቸው ግራ እንደተጋቡ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር በጽዮን ንጉስ ከሆነ ለምን እርሱ እኛን አላዳነንም?” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በተቀረጹ ምስሎቻቸውና እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ጣዖታት እኔን ለምን አስቆጡኝ?

“እኔን” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ ይህ ጥያቄ በዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እኔ እንዳድናቸው የሚፈልጉ ከሆነ በተቀረጹ ምስሎቻቸው እኔን ሊያስቆጡኝ አይገባም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )