am_tn/jer/08/16.md

3.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለሚመጣው ቅጣት መልእክቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “የእርሱ” እና “እነርሱ” የሚሉት ቃላት የይሁዳ ጠላቶችን ያመለክታል፡፡

የፈረሶቹ ፉርፉርታ ከዳን ተሰማ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የፈረሶቹን ፉርፉርታ የዳን ሕዝብ ሰምተውታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ፌርፉርታ

ፈረስ በአፍንጫው የሚያሰማው ከፍ ያለ ድምጽ

ፈረሶች

ጎልማሳ ወንዶች ፈረሶች

ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች

ይህ ግነት ሲሆን የይሁዳ ሕዝብ በፍርሃት ለመንቀጥቀጣቸው ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- የምድሪቱ ሕዝቦች በሙሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ” (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በጠንካራ ፈረሶቹ የማሽካካት ድምጽ

“የጠላትን ጠንካራ ፈረሶች ድምጽ በሰሙ ጊዜ”

ማሽካካት

ፈረስነየሚያሰማው ድምጽ

እነርሱ ይመጡና ይውጡአችኋል

እዚህ ላይ “ይውጡአችኋል” የሚለው ቃል መብላት ማት ነው፡፡ ይህ ጠላቶች እንዴት እንደሚመጡና ምድሪቱንና በእርሷ የሚኖሩትን ሰዎች እንደሚያጠፉ የሚያሳይ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ይመጡነና ያጠፉአችኋል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከቱ

“አሁን አስተውሉ”

እኔ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦች፣ በአስማት ብልሃት ልትከለክሉአቸው የማትችሉአቸውን እፉኝቶች እልክባችኋለሁ

እባቦቹና እፉኝቶቹ የጠላትን ወታደር ይወክላሉ፣ መንከሳቸው ደግሞ የጠላትን ጥቃት ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በመካከላችሁ ከቁጥጥራችሁ በላይ የሆኑ የጠላት ወታደሮችን እልካለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በአስማት ብልሃት ልትከለክሉአቸው የማትችሉአቸውን እፉኝቶች

እዚህ ላይ አስማት ማድረግ የሚለው ሀረግ እባቦችን ለመቆጣጠር መዘመር ወይም ሙዚቃ ማሰማት ነው፡፡

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)