am_tn/jer/08/14.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

የይሁዳ ሕዝብ በሚቀጡበት ጊዜ ምን እንደሚሉ ለእኛ በመንገር እግዚአብሔር መልእክቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

“እኛ”፣ “ለእኛ” እና “የእኛ” የሚሉት ቃላት የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታሉ፡፡

ለምን እዚህ እንቀመጣለን?

ይህ ጥያቄ የተጠየቀው የድርጊት እርምጃን ለማነሳሳት ነው፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እዚህ መቆየት የለብንም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድነት ወደዚህ ኑ፤ ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሂድ

`የተመሸጉ ከተሞች” ከፍተኛ የግንብ አጥር እና ጠንካራ ከለላ የነበራቸው ከተሞች ናቸው፡፡ እነዚህ ተመሳሳይ ሀረጎች በኤርምያስ 4:5 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸቸው ተመልከት፡፡

በዚያ እንሞታለን፣ ድምጻችንንም እናጠፋለን

እዚህ ላይ “ድምጻችንንም እናጠፋለን”የሚለው መሞት ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እዚያ እንሙት” ወይም “በዚያ እንዲገድሉን ጠላቶቻችንን እንጠብቅ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር አምላካችን እንድንጠፋ አድርጎናል

እዚህ ላይ “እንድንጠፋ” የሚለው የሞት ፍርድ እንደተላለፈባቸው የሚያሳይ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አምላካችን የሞት ፍርድ ስላስተላለፈብን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መርዝ እንድንጠጣ ያደርገናል

ይህ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ያስተላለፈውን ፍርድ የሚያሳይ ፈሊጥ ነው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን መልካም ነገር አይኖርም

“ነገር ግን አንድም መልካም ነገር አይሆንም”

ነገር ግን ተመልከቱ

“ነገር ግን አስተውሉ”