am_tn/jer/08/11.md

3.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች “እነርሱ”፣ የእነርሱ” እና ለእነርሱ” የሚሉት ቃላት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

የሕዝቤን ቁስል በጥቂቱ ይፈውሳሉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ቁስል ከኃጢአታቸው የተነሳ የሚገጥማቸውን ችግር የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ችግር ቀለል እንደሆነ ያስባሉ” ወይም 2) ቁስል የሕዝቡን ኃጢአት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ኃጢአት እንደ ትንሽ ቁስል ቀላል እንደሆነ ያስባሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁስልን በጥቂቱ ይፈውሳሉ

እዚህ ላይ “ጥቂት” የሚለው ቃል ቁስል ቀላል እንደሆነና ብዙ አስቸጋሪ እንዳልሆነ አድርገው በማየት ተገቢ እንክብካቤ አለመስጠትን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላም ሳይሆን ‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ

“‘ሁሉም ደህና ነው፣ ሁሉም ደህና ነው’ ይላሉ፣ ነገር ግን ደህና አይደለም”

አስጸያፊ ነገሮችን ሲሰሩ አፍረዋልን?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በኃጢአታቸው ባለማፈራቸው ምክንያት ቁጣውን ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም አስደንጋጭ ኃጢአት ሰርተዋል፣ ነገር ግን ምንም አያፍሩም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እንዴት ማፈር እንዳለባቸው አያውቁም

“ፊታቸው እንኳ ፈጽሞ አልቀላም፡፡” ሰው ሲያፍር ብዙ ጊዜ ፊቱ ይቀላል፡፡

ከሚወድቁት ጋር ይወድቃሉ

እዚህ ላይ “ይወድቃሉ” የሚለው ይገደላሉ የሚለውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተገደሉት ከሌሎቹ ጋር አብረው አንድ ላይ ይገደላሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ

እዚህ ላይ “ይዋረዳሉ” የሚለው መጥፋትን ይወክላል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በምቀጣቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅጠሉ ይረግፋል

“ቅጠሉ ይደርቃል”

እኔ የሰጠኋቸው ሁሉ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል

እዚህ ላይ የመጀመርያው ጽሑፍ ትርጉም ምን እንደሆነ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡