am_tn/jer/08/06.md

3.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እነርሱ” እና “ለእነርሱ” የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት የይሁዳ ሕዝብን ነው፡፡

አደመጥሁ ሰማሁም

እነዚህ ሁለት ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ( ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛውን ነገር አይናገሩም

“ትክክለኛውን ነገር አይሉም”

ስለ ክፋቱ

“ክፋት” የሚለው ረቂቅ ስም “ክፉ” የሚለውን ቅጽል በመጠቀም መተርጎም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ በመሆኑ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ምን አድርጌአለሁ?

ይህ አመልካች መረጃ የሚያሳየው ይህ ጥያቄ የይሁዳ ሕዝብ ሊጠይቀው የሚገባ እንደነበር ነው፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ክፉ ስራ ሰርቻለሁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ወደፈለጉት ይሄዳሉ

“በራሳቸው መንገድ ይሄዳሉ”

ወደ ጦርነት እንደሚሮጥ ፈረስ

ሕዝቡ የራሳቸውን መንገድ ለመከተል የነበራቸው ጉጉት ወደ ጦርነት ለመሮጥ ከተዘጋጀ ፈረስ ጉጉት ጋር ተነጻጽሯል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፈረስ

ወንድ ጎልማሳ ፈረስ

ሽመላ እንኳ በሰማይ የተወሰነ ጊዜዋን ታውቃለች፤ ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳም

ይህ አመልካች መረጃ የሚያሳየው እንደነዚህ የመሳሰሉ አእዋፍ የሚሰደዱበትን ማለትም በተለያዩ የዓመቱ ወቅት ምግብ ለመፈለግና ለመባዛት ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ የሚጓዙበትን ትክክለኛ ጊዜ እንደሚያውቁ ነው፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሽመላ … ዋኖስ፣ ጨረባና ዋርዳ

እነዚህ በሙሉ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚሰደዱ የተለያዩ ዓይነት አእዋፍ ናቸው፡፡ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በትክክለኛው ጊዜ ወደ ስደት ይሄዳሉ፤ ነገር ግን ሕዝቤ የእግዚአብሔርን ስርዓት አያውቁም፡፡

ይህ አመልካች መረጃ የሚያሳየው ሕዝቡ በተፈጥሮ የእግዚአብሔርን ስርዓት ማወቅ እንደነበረባቸው ነው፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ስደታቸው ይሄዳሉ

“ስደት” የሚለው ረቂቅ ስም “ተሰደዱ” በሚለው ግስ በመጠቀም መተርጎም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ይሰደዳሉ” ወይም “ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ይበርራሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)