am_tn/jer/08/01.md

3.8 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በዚያን ጊዜ

በኤርምያስ 7:32 እስከ 34 ውሰጥ ያሉት ክስተቶች በሚፈጸሙበት ጊዜ፡፡

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ያመጡአቸዋል

እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የይሁዳን ሕዝብ ጠላቶች ይወክላል፡፡

መኳንንቶቻቸው

“ነገስታቶቻቸው” ወይም “መሪዎቻቸው”

እነርሱን ይዘረጉአቸዋል

“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው በቀደመው ጥቅስ የተዘረዘሩትን ሰዎች አጥንቶች ነው፡፡

እነርሱ በተከተሏቸውና በአገለገሏቸው እንዲሁም አብረው በተጓዟቸውና በፈለጓቸው፣ ባመለኳቸው

እዚህ ላይ “እነርሱ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን የሚያመለክት ነው፡፡ እነዚህ ሦስት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡

አብረው በተጓዟቸው

ይህ ለማገልገልና ለማምለክ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 2:23 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አጥንቶች አይሰበሰቡም ወይም እንደገና አይቀበሩም

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አጥንቶቻቸውን ማንም ሰው አይሰበስበውም ወይም እንደገና አይቀብሯቸውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ተጣለ ጉድፍ በምድር ገጽ ላይ ይበተናል

አጥንቶች በምድር ላይ ካለ ጉድፍ ተነጻጽረዋል፣ ይህ ንጽጽር አጥንቶቹ አስጸያፊ እንደሚሆኑና እንደገና እንደማይቀበሩ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምድረ ገጽ ላይ

“በምድር ዙርያ ሁሉ”

እነርሱን ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ

“እነርሱን” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳ ሕዝብን ነው፡፡

ከዚህ ክፉ ሕዝብ አሁንም የቀሩት ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ለራሳቸው ሞትን ይመርጣሉ

“ከዚህ ክፉ ሕዝብ የቀሩት ሁሉ በሕይወት ከሚኖሩ መሞት ይፈልጋሉ”

ይህ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ተመሳሳይ ቃላትን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)