am_tn/jer/07/33.md

1.8 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያመጣውን ፍርድ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አስከሬኖች

“የሞቱ አካላት”

ይህ ሕዝብ

“የይሁዳ ሕዝብ”

የሰማይ ወፎች

“የሰማያት ወፎች” የሚለውን በኤርምያስ 4:25 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

የምድር አውሬዎች

“የምድሪቱ የዱር እንስሳት”

የሚያባርራቸው

“የሚያስፈራራቸው”

አጠፋለሁ

“አስወግዳለሁ”

የደስታ ድምጽና የተድላ ድምጽ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ሙሉ በሙሉ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ “ደስታ” እና “ተድላ” የሚሉት ረቂቅ ስሞች “መደሰት” በሚለው ግስ እና “ደስተኛ” በሚለው” ቅጽል በመmጠቀም ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚደሰቱ እና የደስተኛ ሰዎች ድምጽ” (ጥምር ቃል የሚለውን እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የሙሽራ ድምጽ እና የሙሽሪት ድምጽ

ይህ በሰርግ ስነ ስርዓት ላይ ለሚከናወኑ ነገሮች ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰርግ ስነ ስርዓት የሚያከብሩ ሰዎች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ባድማ ትሆናለች

“ባድማ” የሚለው ረቂቅ ስም “ሰው የማይኖርበት” በሚለው ቅጽል በመጠቀም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው የማይኖርባት ትሆናለች” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)