am_tn/jer/07/31.md

3.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ የሰራቸውን ክፉ ነገሮች መግለጹን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እነርሱ” እና “የእነርሱ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

የቶፌት ከፍተኛ ስፍራዎች

ይህ የእስራኤል ሕዝብ ልጆቻቸውን በእሳት በማቃጠል ለሐሰተኛ አማልክት መስዋዕት አድርገው ያቀረቡበት የቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የቤን ሄኖም ሸለቆ

ይህ ሕዝቡ ለሐሰተኛ አማልክት መስዋዕት ያቀረቡበት ከኢየሩሳሌም ከተማ በደቡብ በኩል የሚገኝ የሸለቆ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በእሳት

ይህ አመልካች መረጃ ለሐሰተኛ አማልክት እንደ መስዋዕት ይቃጠሉ እንደነበር የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ መስዋዕት” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከቶ በአእምሮየ ያለሰብሁትን

እዚህ ላይ “አእምሮ” የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ሃሳብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከቶ ስለዚህ ነገር ፈጽሞ አላሰብሁም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህ ተመልከቱ

እዚህ ላይ “ተመልከቱ” የሚለው ቃል ለሚከተለው ነገር አጽንዖትን ይጨምራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእርግጥ”

የማይባልበት ቀናቶች ይመጣሉ

የወደፊት ጊዜ “ቀናቶች እየመጡ እንደሆነ” ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለወደፊት እንዲህ የማይባልበት” ወይም “እንዲህ የማይባልበት ጊዜ ይኖራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ወዲህ … ተብሎ አይጠራም

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ከእንግዲህ እንዲህ … ብለው አይጠሩትም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

አስከሬኖች ይቀብራሉ

“የሞቱ ሰዎችን ይቀብራሉ”

የሚቀር ምንም ክፍል የለም

“የሚቀር ምንም ቦታ የለም”