am_tn/jer/07/27.md

2.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ያለውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ለእነርሱ” እና “እነርሱ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

ስለዚህ እነዚህን ቃላት በሙሉ ለእነርሱ ትናገራለህ ነገር ግን አንተን አይሰሙህም፡፡ እነዚህን ነገሮች ለእነርሱ ትናገራለህ ነገር ግን ለአንተ አይመልስሉህም፡፡

እነዚህ ሁለት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ሃሳብ አላቸው፣ ሁለተኛው ለመጀመርያው መልእክት አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔን መልእክት ንገራቸው ነገር ግን እነርሱ አንተን አይሰሙህም ለአንተም አይመልሱልህም” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

የአምላኩ የእግዚአብሔር ድምጽ

እዚህ ላይ “የአምላኩ የእግዚአብሔር ድምጽ” የሚለው እግዚአብሔር የተናገረውን ይወክላል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡25 ላይ እንዴት እንደተረገምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አምላኩ እግዚአብሔር የተናገረው ነገር” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል

እግዚአብሔር ስለ እውነት ሲናገር ሕዝቡ ሊያጠፉት የሚችሉትና መነገሩንም ሊያስቆሙት የሚችሉት ነገር እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቡ እውነትን አጥፍተዋል፣ ከአፋቸውም ቆርጠውታል” ወይም “ሕዝቡ ውሸት ብቻ ይናገራሉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እውነት ጠፍቶአል

“እውነት” የሚለው ረቂቅ ስም “እውነተኛ” በሚለው ቅጽል በመጠቀም ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እውነተኛ የሆነው ነገር ጠፍቶአል” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)