1.9 KiB
1.9 KiB
አያያዥ ሀሳብ፡-
እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ያለውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡
አጠቃላይ መረጃ፡-
በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡
የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል
ኤርምያስ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም ጠቃሚ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 6:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡
የሚቃጠለውን መስዋዕታችሁን በሌሎች መስዋዕታችሁ ላይ ጨምሩ፣ ስጋውንም ራሳችሁ ብሉ
ይህ መስዋዕታቸው በሙሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አጽንዖት የሚሰጥ ምጸታዊ ዓረፍተ ሃሳብ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሂዱና የሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁን ከመስዋዕታችሁና ከስጋው ጋር አብራችሁ ብሉት” (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
ድምጼን ስሙ
እዚህ ላይ የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማት ቃሉን መስማትና ለተናገረው ደግሞ መታዘዝ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተናገርሁትን ስሙ ደግሞም ታዘዙ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)
ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ
እግዚአብሔር ቃሉን ስለመታዘዝ ሲናገር ሰው በመንገድ እንደሚሄድ እንደዚሁ አንድ ሰው በቃሉ መሄድ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ አድርጉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)