am_tn/jer/07/19.md

3.6 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ለኤርምያስ መናገር ቀጥለሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች “እነርሱ” እና “ራሳቸው” የሚሉት የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታል፡፡

በእውነት እነርሱ እኔን ያስቆጡኛልን?

ይህ ጥያቄ አሉታዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ በእርግጥ ሊያስቆጡኝ አይችሉም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

ኤርምያስና የይሁዳ ሕዝብ እርሱ የሚናገረውን ነገር በጥንቃቄ ይሰሙ ዘንድ እግዚአብሔር ስለራሱ ሲናገር ሌላ ሰው እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህንን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያወጀው ይህን ነው” ወይም “ “እግዚአብሔር የተናገረው ይህን ነው” (ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እፍረታቸው በራሳቸው ላይ ይሆን ዘንድ እኔን ያስቆጡኝ አነርሱ ራሳቸው ኤደሉምን?

ይህ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ ይጠብቃል፡፡ ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እፍረታቸው በራሳቸው ላይ ይሆን ዘንድ ራሳቸውን እያስቆጡ ነው” ወይም “እነርሱ ራሳቸውን ችግር ውስጥ እያስገቡና በራሳቸው ላይ እፍረት እያመጡ ነው!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እፍረት በእነርሱ ላይ ነው

“እፍረት” የሚለው ረቂቅ ስም “አፈሩ” በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አፈሩ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከት

ይህ ቃል እዚህ ላይ የአንድ ሰውን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚነገረው ቁም ነገር ለመሳብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድምጥ” ወይም “እኔ ለአንተ ለምነግርህ ነገር ትኩረት ስጥ”

ቁጣየና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይጎርፋል

እግዚአብሔር ስለ ቁጣው ሲገልጽ ሊፈስ የሚችል ነገር እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ይህን ስፍራ እቀጣለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣና መዓት

እነዚህ ቃላቶች በመሰረታዊነት ተመሳሳይነት ያላቸው ሲሆኑ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጥልቀት አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

አጎርፋለሁ

“አፈስሳለሁ”

ይነድዳል ደግሞም አይጠፋም

እግዚአብሔር ስለ ቁጣው ሲናገር ቁጣው ሊጠፋ የማይችል እሳት እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቁጣየን አንድም ሰው ሊያስቆመው አይችልም” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ፈጽሞ አይጠፋም

“ፈጽሞ መንደድ አይቆምም”