am_tn/jer/07/16.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ለኤርምያስ ይነግረዋል፡፡ በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “ይህ ሕዝብ” የሚለው የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታል፡፡

ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፣ የልቅሶ ልመና ወደ እኔ አታቅርብ ወይም እነርሱን ወክለህ ጸሎት አታድርግ፣ ወደ እኔ አቤቱታ አታቅርብ

እነዚህ አራት ነገሮች እያንዳንዱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የተደጋገሙት አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

የልቅሶ ልመና ማቅረብ

“በሃዘን መጮህ”

እነርሱን ወክለህ

“ለእነርሱ ጥቅም” ወይም “ለእነርሱ”

አቤቱታ ወደ እኔ ማቅረብ

“ወደ እኔ መማለድ”

በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ምን እንደሚሰሩ አትመለከትምን?

ይህ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ ይጠብቃል፤ ጥያቄው የተጠየቀው እነዚህን ነገሮች በኤርምያስ ዘንድ ትኩረት እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡ ይህ እንደ አረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ምን እንደሚሰሩ ተመልከት!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እሳቱን ማንደድ

“እሳቱን መጀመር”

ዱቄት ይለውሳሉ

በእጅ ሊጥ ማዋሃድ

ሊጥ

ለመጋገር የሚጠቅም የዱቄትና የፈሳሽ ወፍራም ውህድ

የሰማያት ንግስት

ይህ የሐሰተኛ አምላክ ስም ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “‘የሰማያት ንግስት’ የምትባል ሐሰተኛ አምላክ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን ያናድዳሉ

“እኔን ያስቆጣሉ”