am_tn/jer/07/12.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚያስተላልፈውን መልእክት ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ ያሉት “እናንተ” እና “የእናንተ” የሚሉት ቃላቶች የይሁዳን ሕዝብ ያመለክታሉ፡፡

በቀድሞ ዘመን ስሜ እንዲያድርበት ወደፈቀድሁበት በሴሎ ወደነበረው ስፍራ ሂዱ

እዚህ ላይ “ስሜ እንዲያድርበት ወደፈቀድሁበት” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ይህ ስፍራ እግዚአብሔር ይመለክበት የነበረ ነው የሚል ትርጉም አለው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀድሞ ሕዝቤ እኔን ለማምለክ እኔ ወደፈቀድሁበት በሴሎ ወዳለው ስፍራ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስላደረጋችሁ

“ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስታደርጉ ስለነበራችሁ”

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደገና ደግሜ ደጋግሜ

እነዚህ ሁለት የተጣመሩ ስሞች ፈሊጥ ሲሆኑ አንድ ነገር ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ተደርጓል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተደጋጋሚ” ወይም “ያለማቋረጥ” (ጥምር ቃል እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ በስሜ የተጠራው ቤት

ይህ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምትክ ስም ነው፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይሀንን በኤርምያስ 7፡10 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ የሆነው ይህ ቤት” ወይም “እኔን የምታመልኩበት ይህ ቤተ መቅደስ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)