am_tn/jer/07/08.md

4.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚነገረውን መልእክቱን ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ “እናንተ” የሚለው ቃል የይሁዳ ሕዝብን ያመለክታል፡፡

እነሆ!

እዚህ ላይ “እነሆ” የሚለው ቃል ከዚህ በኋላ የሚከተለውን መረጃ እንደሚገባ ልብ እንድንል ያነቃናል፡፡

ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ? በሐሰትም ትምላላችሁ፥ … የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ?

እየፈጸሟቸው ያሉትን ኃጢአቶች እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ እንደ አረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፡፡ በሐሰት ትምላላችሁ፥ … የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በሐሰት ትምላላችሁ

“በመኃላችሁ እንኳ ትዋሻላችሁ”

እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ

እዚህ ላይ መከተል ለማገልገልና ለመታዘዝ ዓላማ በማድረግ ተከትሎ ለመሄድ ምትክ ስም ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 7:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች አማልክት ታገለግላላችሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ መጥታችሁ በፊቴ ትቆሙና … እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ታደርጋላችሁ?

በቃልና በድርጊት የሚፈጽሙትን ግብዝነት እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ እንደ አረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደዚያ ከሆነ መጥታችሁ በፊቴ ትቆማላችሁ … እነዚህን አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ ታደርጋላችሁ፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በስሜ በሚጠራው ቤት

ይህ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ የሆነው ቤት” ወይም “እኔን የምታመልኩበት ቤተ መቅደስ” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ በስሜ የሚጠራው ቤት በእናንተ ዓይን የወንበዴዎች ዋሻ ሆኖአልን?

እነርሱ ስለ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ምን እንደሚያስቡ እግዚአብሔር የሚያውቅ መሆኑን አስረግጦ ለማለፍ እነዚህ ጥያቄዎች አዎንታዊ መልስ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ በዓረፍተ ሃሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስሜን የተሸከመው ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የወንበዴዎች ዋሻ ነው!” ወይም “በስሜ የተጠራው ይህ ቤት ወንበዴዎች ሊሔዱና ሊሸሸጉ የሚችሉበት ስፍራ እንደሆነ የምታስቡ ትመሰስላላችሁ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ስሜን የተሸከመው ይህ ቤት

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔርን ስም እንደተሸከመ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ ይህ ከዚህ በፊት ካው ጥቅስ “በስሜ በተጠራው ይህ ቤት” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንበዴዎች

የሚሰርቁና የሚዘርፉ ሃይለኛ ሰዎች

ነገር ግን እነሆ አይቻለሁ

“ነገር ግን እኔ በእርግጠኝነት እናንተ የምትሰሩት ምን እንደሆነ ተመልክቻለሁ”

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)