am_tn/jer/07/05.md

2.1 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚነገረውን መልእክቱን ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

መንገዳችሁንና ስራችሁን አሳምሩ

“መንገዳችሁንና ስራችሁን አስተካክሉ፡፡” ይህንን በኤርምያስ 7:3 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ ፍትህ አድርጉ

“ፍትህ” የሚለው ረቂቅ ስም “ፍረዱ” በሚለው ግስ በመጠቀም መተርጎም ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በትክክል ፍረዱ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መጻተኛውን አትጨቁኑ

“መጻተኛውን በአግባቡ ያዙ”

ወላጅ አልባ

ወላጆቹ የሞቱበት ልጅ

ንጹህ ደም ባታፈስሱ

እዚህ ላይ ንጹህ ደም ማፍሰስ ሞት የማይገባቸውን ሰዎች መግደልን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ንጹህ ሰዎችን መግደል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ሌሎች አማልክት መከተል

እዚህ ላይ መከተል የሚለው ለማገልገልና ለመታዘዝ ዓላማ አድርጎ ተከትሎ ለመሄድ ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሌሎች አማልክትን ማገልገል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እናተን የሚጎዷችሁ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚያ እናንተን ይጎዷችኋልና” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ ስፍራ

እዚህ ላይ “በዚህ ስፍራ” የሚለው የይሁዳን ምድር ያመለክታል፡፡

አኖራችኋለሁ

“መኖር እንድትቀጥሉ አደርጋችኋለሁ”

ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘላለም

“ከጥንት ጀምሮ እንዲሁም በቀጣይነት፡፡” የእነርሱ ቋሚ ንብረት ትሆን ዘንድ እግዚአብሔር ምድሪቱን ለይሁዳ ሕዝብ ሰጥቷል ማለት ነው፡፡