am_tn/jer/07/03.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ የሚነገረውን መልእክቱን ለኤርምያስ መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

ኤርምያስ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም ጠቃሚ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 6:6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡

መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ እኔም እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ

“መንገዳችሁንና ሥራችሁን የምታስተካሉ ከሆነ እኔም እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ

በዚህ ስፍራ

ይህ በይሁዳ ምድር ማለት ነው፣ በቤተ መቅደስ አይደለም

እያላችሁ ራሳችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ

ይህ “ራሳችሁ” የሚለው ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም ለእስራኤላውያን ወደፊት የሚመጣ የግል አደጋ እንዳለ አጽንዖት የሚሰጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያላችሁ፣ እናንተን እንዲጠብቃችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ” (ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ!የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ! የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ!

ቤተ መቅደሱ ባለቤቱ እግዚአብሔር ስለሆነና የእርሱን ሕልውና የሚወክል ስለሆነ እርሱ ይጠብቀዋል፣ የይሁዳም ሕዝብ ደህንነት ይሆንለታል፡፡ “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ” የሚለው ለምን ሦስት ጊዜ እንደተደጋገመ ተቀባይነት ሊኖራቸው የሚችሉት ትርጉሞች የሚከተሉት ናቸው፡- 1) የተደጋገመው አጽንዖት ለመስጠት ነው ወይም 2) የተደጋጋመው እንደ ቤተ መቅደሱ ስነ ስርአት ተደርጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው ስለዚህ አንድም ሰው ሊያፈርሰው እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኞች ነን፤ እኛ ደግም እንጠበቃለን፡፡” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)