am_tn/jer/06/25.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስ ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ይናገራል፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እየተናገረ ነው ብለው ተርጉመውታል፡፡

የጠላት ሰይፍና ድንጋጤ ከብቧችኋል

“የጠላት ሰይፍ” የሚለው ሀረግ ከሰይፎቻቸው ጋር ለማጥቃት የተዘጋጁ ጠላቶችን ይወክላል፡፡ “ድንጋጤ” የሚለው ረቂቅ ስም ሰዎች እንዲፈሩ የሚያደርጉ ነገሮችን ያመለክታል፡፡ ይህ ደግሞ ከቅጽል ጋር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች ከሰይፎቻቸው ጋር በሁሉም ስፍራ ስላሉ እያንዳንዱ ሰው በፍርሃት ይንቀጠቀጣል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ and ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የሕዝቤ ሴት ልጅ

እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንደ ሴት ጠርቶ በመናገር ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ኤርምያስ ያሳያል፡፡ ይህን ተመሳሳይ ሀረግ በኤርምያስ 4:11 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ “እናንተ ለእኔ እንደ ሴት ልጅ የሆናችሁ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማቅ ልበሺ በአመድም ላይ ተንከባለይ

ሕዝብ እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው ከመጠን በላይ የሆነ ሃዘን እንደተሰማቸው ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማቅ በመልበስና በአመድ ላይ በመንከባለል ከመጠን በላይ እንዳዘንሽ አሳዪ” (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንድያ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ፣ መራራ ልቅሶ አልቅሺ

ኤርምያስ የሕዝቡን ታላቅ ሃዘን እናት አንድያ ልጇ ሲሞትባት ከሚሰማት ሃዘን ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንድያ ልጅሽ እንደሞተባት እናት ሆነሽ መራራ ልቅሶ አልቅሺ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አጥፊው በድንገት በላያችን ይመጣልና

“ምክንያቱም የጠላት ጦር ሰራዊት እኛን ለማጥቃት በድንገት ይመጣልና”