am_tn/jer/06/23.md

2.1 KiB

ቀስትና ጦር ይዘዋል

“ወታደሮቹ ቀስትና ጦር ይይዛሉ”

ድምጻቸው እንደተናወጠ ባህር ነው

ወታደሮቹ የሚኖራቸው ትልቅ ድምጽ ከባህር ከሚነሳው ታላቅ ድምጽ ጋር ተነጻጽሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የጩኸታቸው ድምጽ በጣም ከፍተኛ ነው፣ እንደ ባህር ድምጽ ነው” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በፈረሶች ላይ ሆነው ይጋልባሉ፣ ለጦር እንደተዘጋጀ ሰው ተሰለፉ

“ተሰለፉ” የሚለው ራሳቸውን አቀናጅተዋል፣ ፈረሶቻቸውን በሰልፍ ይጋልባሉ ማት ነው፡፡ “ለጦር እንደተዘጋጀ ሰው” የሚለው ለመዋጋት መዘጋጀታቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተመደበላቸው ሰልፍ ፈረሶቻቸውን ይጋልባሉ፣ እናንተን ለመዋጋት ተዘጋጅተዋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ ሰምተናል

“እኛ” የሚለው ምናልባት ኤርምያስንና የይሁዳ ሕዝብን ሳያመለክት አይቀርም፡፡

እጃችን በጭንቀት ደክማለች

“እጆቻችን ከጭንቀት የተነሳ ደክመዋል”

ጭንቀት ይዞናል

የነበራቸው ከፍተኛ የጭንቀት ስሜት ሲገለጽ ጭንቀቱ እንደያዛቸው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም አስደንጋጭ ጭንቀት ይሰማናል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ልጅ እንደምትወልድ ሴት

ጠላት እነርሱን ለማጥቃት ከመምጣቱ የተነሳ የተሰማቸው ጭንቀት አንዲት ሴት ልጅ ለመውለድ ምጥ ሲይዛት ከሚሰማት ስሜት ጋር ተነጻጽሯል፡፡ አማራጭ “ልጅ ለመውለድ እንደምታምጥ ሴት” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)