am_tn/jer/06/20.md

3.1 KiB

ዕጣን ከሳባ ምድር፣ ጣፋጭ ቅመም ከሩቅ አገር ቢመጣ ምን ይጠቅመmኛል?

እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመገሰጽ እነዚህን ጥያቄዎች ይጠቀማል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ዕጣን ከሳባ ምድርና ከሩቅ አገር የሚመጣው ጣፋጭ ቅመም ለእኔ ምንም አይጠቅመኝም፡፡” ወይም “ከሩቅ አገር የመጣው የቅመማችሁ ጣፋጭ ሽታ አልፈልገውም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ጣፋጭ ሽታዎች

ሰዎች ጣፋጭ ሽታ ያላቸው ቅመሞችን ለእግዚአብሔር እንደ መስዋእት ያቃጥሉ ነበር፡፡

በእኔ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም

“እኔን አያስደስተኝም” ወይም “እኔን ደስ አያሰኘኝም”

ተመልከቱ፣ እኔ

“አስተውሉ፣ ምክንያቱም እኔ የምናገረው እውነት በጣም ጠቃሚ ነው፣ እኔ”

በዚህ ሕዝብ ላይ መሰናክልን አስቀምጣለሁ

“በዚህ ሕዝብ ፊት ለፊት መሰናክል አስቀምጣለሁ፡፡” እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመጣ ስለሚያደርገው ችግር ሲናገር ሰዎች ተደናቅፈው የሚወድቁበት እንቅፋት አድርጎ ገልጾታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በዚያ ላይ ይደናቀፋሉ

እዚህ ላይ “ይደናቀፋሉ” የሚለው በችግሮቹ ምክንያት እንደሚጎዱ የሚያሳይ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድ ላይ

“ይደናቀፋሉ” የሚለውን ሃሳብ ከቀደመው ቃል መረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድ ላይ ይደናቀፋሉ” ወይም “አባቶችና ወንዶች ልጆች በአንድ ላይ ይጎዳሉ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው

“ጎረቤቶችና ጓደኞቻቸው”

ሕዝብ እየመጣ ነው

የእነርሱ ዓላማ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝብ እናተን ለማጥቃት እየመጣ ነው” ወይም “ጦር ሰራዊት እየመጣ ነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ ሕዝብ

እዚህ ላይ “ሕዝብ” የሚለው የሕዝቡን ጦር ሰራዊት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የታላቅ ሕዝብ ጦር ሰራዊት” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምድሪቱ ሩቅ ክፍል እየተነሳሳ ነው

“እየተነሳሳ” የሚለው አንድን ነገር ለማድረግ መዘጋጀትን የሚወክል ነው፡፡ ማራጭ ትርጉም፡- “ከምድሪቱ ሩቅ ክፍል ለመምጣት እየተዘጋጀ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)