am_tn/jer/06/16.md

6.2 KiB

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል

እግዚአብሔር ይህን ለማን እንደሚናር በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ይህን የሚናገረው ለእስራኤል ሕዝብ ነው” ወይም “እግዚአብሔር ይህን የሚናገረው ለሕዝቡ ነው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንታ መንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም … በእርሷ አንሄድባትም

መንገድ ሰዎች የሚኖሩበትን የሕይወት ዘይቤ የሚያመለክት ነው፡፡ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ሕይወታቸውን የሚኖሩበትን መልካሚቱን የሕይወት መንገድ ምን እንደሆነች እንዲጠይቁና በዚያ መንገድ እንዲኖሩ መጠየቅ ይፈልጋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መንታ መንገድ

ይህ ሁለት መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ ያመለክታል፡፡

የቀደመችውን መንገድ ጠይቁ

የቀደመችው መንገድ የአባቶቻቸውን ባህርይ፣ ከረጅም ጊዜ በፊት አባቶቻቸው እንዴት እንደኖሩ የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቶቻችሁ ስለሄዱበት መንገድ ጠይቁ” ወይም “አባቶቻችሁ እንዴት እንደኖሩ ጠይቁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ መልካም መንገድ ወዴት ነው?

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) “ይህ መልካም መንገድ” ሊኖሩበት የሚገባውን መልካም የሕይወት መንገድ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልንርበት የሚገባ ይህ መልካም መንገድ ወዴት አለ?” ወይም 2) “ይህ መልካም መንገድ” በረከት የሚያመጣውን የሕይወት መንገድ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መልካ ወደሆነው ነገር የሚወስደን መንገድ ወዴት አለ” ወይም “ልንኖርበት የሚገባ በረከት የሚያመጣው መንገድ ወዴት አለ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንግዲያው በእርሷ ሂዱ

“እንግዲያው በዚያች መንገድ ሂዱ፡፡” በዚያች መንገድ መሄድ በዚያች መንገድ መኖርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንግዲያው በዚያ መንገድ ኑሩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ አንሄድም

ይህ በዚያች መንገድ አለመኖርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ በዚያች መንገድ አንኖርም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የመለከት ድምፅን እንድትሰሙ ጠባቂዎችን አቆምሁላችሁ

እግዚአብሔር በአደጋ ላይ ያሉትን ሕዝብ ለማስጠንቀቅ ነቢያቱ የተላኩ ጠባቂዎች እንደሆኑ አድርጎ ይናራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእናንተ አቆምሁላችሁ

“እናንተ” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ ያመክለታል፡፡

መለከቱን እንድትሰሙ

“የመለከቱን ድምጽ እንድትሰሙ፡፡” እግዚአብሔር ለነቢያቱ ስለሰጠው የማስጠንቀቂያ መልእክት ሲናገር መልእክቱ ስለሚመጣው አደጋ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ የሚነፋ መለከት እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ ነቢያቱ ይህንን ማስጠንቀቂያ ሊሰሙና ስለሁኔታው ለሕዝቡ ሊናገሩ ይገባል፡፡

እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ! እናተ ምስክሮች ሕዝቡ ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ፣ ምድር! ተመልከቺ

እነዚህ ሦስት አረፍተ ነገሮች በሙሉ እግዚአብሔር በአመጸኛው በይሁዳ ሕዝብ ላይ የሚያደርገውን ነገር ምስክር እንዲሆኑ ለሌሎች መንግስታት ሕዝቦች የሚናገሩ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ሌሎች ሕዝቦች፣ በሕዝቤ ላይ የማደርገውን ነገር ተመልከቱ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና እንቶኔ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ!

“እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ፣ እኔ የምናገረውን ስሙ”

እኔ በዚህ ሕዝብ ላይ ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ

“በቅርቡ ይህን ሕዝብ በጽኑ እቀጣዋለሁ”

እናንተ ምስክሮች

“እናተ ምስክሮች የሆናችሁ”

በእነርሱ ላይ ምን እንደሚሆን

“እነርሱ” የሚለው ቃል የእስራኤልን ሕዝብ ይወክላል፡፡

ምድር ስሚ

“ምድር” የሚለው ቃል በምድር የሚኖሩትን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ስሙ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የሃሳባቸው ፍሬ

እዚህ ላይ “ፍሬ” የሚለው ቃል የሚያስከትለውን ውጤት ወይም መዘዝ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሃሳባቸው የሚያስከትለው መዘዝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለቃሌ ወይም ለሕጌ ትኩረት ስላልሰጡ ይልቁንም ደግሞ ስላልተቀበሉት

እዚህ ላይ “ለቃሌ ትኩረት ስላልሰጡት” የሚለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር አለመስማታቸውን የሚያመለክት ሲሆን “ስላልተቀበሉት” የሚለው ደግሞ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመታዘዝ አለመፈለጋቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የተናገርሁትን አይሰሙም፡፡ ይልቁንም ሕጌን አልታዘዙም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)