am_tn/jer/06/13.md

4.4 KiB

ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉም ስስታሞች ናቸው

“ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ” የሚለው ሀረግ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ያለምንም ደረጃ ልዩነት “ሁሉ” በሚለው ቃል ውስጥ መካተታቸው የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁሉም፣ አነስተኛ ስልጣን ያለው ጨምሮ፣ እያንዳዱ ሰው ስስታም ነው” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ታናሽ

ይህ አነስተኛ ስልጣን ያላቸውንና በሰዎች ፊት ብዙ ተቀባይነት የሌላቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አነስተኛ ኃይል ያላቸው ሰዎች” (የስም ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ

ይህ ከፍተኛ ስልጣንና ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው ሰዎች” ወይም “በጣም ኃይለኛ የሆኑ ሰዎች” (የስም ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም

“የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ”

ተገቢ ላልሆነ ጥቅም ሲሉ ስስታሞች ናቸው

“ጥቅም” የሚለው ረቂቅ ስም “የበለጠ ገንዘብ ማግኘት” ወይም “የበለጠ ቁሳቁሶች ማግኘት” በሚለው ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች ውሸትን በመናገር የበለጠ ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ” ወይም “የበለጠ ቁሳቁሶችን ማግኘት በጥብቅ ይፈልጋሉ፣ ከዚህ የተነሳ ይህን ለማግኘት ሲሉ ሰዎችን ያታልላሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም ተንኮል ያደርጋሉ

“ሁሉም ሰዎችን ያታልላሉ” ወይም “ሁሉም ውሸታሞች ናቸው”

የሕዝቤን ቁስል በጥቂቱ ይፈውሳሉ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ቁስል ከኃጢአታቸው የተነሳ የሚገጥማቸውን ችግር የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ችግር ቀለል እንደሆነ ያስባሉ” ወይም 2) ቁስል የሕዝቡን ኃጢአት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሕዝቤ ኃጢአት እንደ ትንሽ ቁስል ቀላል እንደሆነ ያስባሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁስልን በጥቂቱ ይፈውሳሉ

እዚህ ላይ “ጥቂት” የሚለው ቃል ቁስል ቀላል እንደሆነና ብዙ አስቸጋሪ እንዳልሆነ አድርገው በማየት ተገቢ እንክብካቤ አለመስጠትን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላም ሳይሆን ‘ሰላም፣ ሰላም’ ይላሉ

“‘ሁሉም ደህና ነው፣ ሁሉም ደህና ነው’ ይላሉ፣ ነገር ግን ደህና አይደለም”

አስጸያፊ ነገሮችን ሲሰሩ አፍረዋልን?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በኃጢአታቸው ባለማፈራቸው ምክንያት ቁጣውን ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም አስደንጋጭ ኃጢአት ሰርተዋል፣ ነገር ግን ምንም አያፍሩም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እንዴት ማፈር እንዳለባቸው አያውቁም

ሰው ሲያፍር ብዙ ጊዜ ፊቱ ይቀላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ፊታቸው እንኳ ፈጽሞ አልቀላም”

ከሚወድቁት ጋር ይወድቃሉ

እዚህ ላይ “ይወድቃሉ” የሚለው ይገደላሉ የሚለውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተገደሉት ጋር አብረው አንድ ላይ ይገደላሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምቀጣቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ

እዚህ ላይ “ይዋረዳሉ” የሚለው መጥፋትን ይወክላል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምቀጣቸው ጊዜ አጠፋቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)