am_tn/jer/06/11.md

4.6 KiB

ነገር ግን እኔ በእግዚአብሔር ቁጣ ተሞልቻለሁ

ይህን የሚናገረው ኤርምያስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተሰማውን ዓይነት ተመሳሳይ ቁጣ ኤርምያስም ተሰምቶታል፡፡ በጣም መቆጣቱን ሲናገር ውስጡ በቁጣ እንደተሞላ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔም እንደ እግዚአብሔር በጣም ተቆጥቻለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ከመታገስ ደክሜአለሁ

ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ቁጣ አለመግለጹ ቁጣውን በራሱ ውስጥ አምቆ እንደያዘው አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይህን ቁጣ ባለመግለጥ እጅግ ደክሜአለሁ” ወይም “ስለዚህ ቁጣ አንዳችም ነገር ባለማድረጌ በጣም ደክሜአለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገድ ላይ በሚገኙ ልጆችና በተሰበሰቡ ወጣቶችም ላይ አፍስሰው

እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ስለመቅጣቱ ሲናገር የእርሱ ቁጣ ኤርምያስ በሕዝቡ ላይ ሊያፈስሰው የፈለገው ፈሳሽ ነገር እነንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመንገድ ላይ የሚገኙትን ልጆችና የተሰበሰቡትን ወጣቶች በቁጣ ቅጣቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር ይወሰዳል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምክንያቱም ጠላቶች እያንዳንዱን ባል ከሚስቱ ጋር ይይዟቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

ረጅም ዓመታት የኖረ እያንዳንዱ ሽማግሌ ይወሰዳል

“ይወሰዳል” የሚለውን ቃል ከቀደመው ሀረግ በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ ዓመታት የኖረ እያንዳንዱ ሽማግሌ ይወሰዳል” ወይም “ብዙ ዓመታት የኖረውን እያንዳንዱ ሽማግሌ እነርሱ ይወስዱታል” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

ረጅም ዓመታት የኖረ እያንዳንዱ ሽማግሌ ይወሰዳል

“ረጅም ዓመታት የኖረ” የሚለው ሀረግ ፈሊጥ ሲሆን ትርጉሙም “በጣም ያረጀ” ማለት ነው፡፡ ይህ “ሽማግሌ” የሚለውን ቃል ያጠናክረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዳንዱ በጣም ያረጀ ሰው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቤቶቻቸው የሌሎች ሰዎች ንብረት ይሆናሉ” ወይም “የእነርሱ ሰዎች ቤቶቻቸውን ይወስዱታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸውን በአንድ ላይ ለሌሎች ይሆናሉ

“ለሌሎች ይሆናሉ” የሚለው ሀረግ ከበፊቱ ሀረግ በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በተጨማሪ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድሪቱን ነዋሪዎች በእጄ አጠቃቸዋለሁ

እዚህ ላይ “እጄ” የሚለው የእግዚአብሔርን ኃይል ይወክላል፡፡ የባዕድ ጦር ሰራዊት እስራኤልን ያጠቃበት ምክንያት እግዚአብሔር ይህን እንዲፈጽሙ ስላደረጋቸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድሪቱ የሚኖሩትን ሰዎች እኔ በራሴ ኃይል አጠቃቸዋለሁ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)