am_tn/jer/06/04.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ከሚያጠቃው ጦር ሰራዊት ወገን የሆነው ንጉስ ከስልጣኑ ስር ላሉት ሰዎች ይናገራል፡፡

ራሳችሁን አቅርቡ

ነገስታቱ ይህን እንደተናገሩ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገስታቱ ለጦር ሰራዊታቸው፣ ራሳችሁን አቅርቡ ብለዋቸዋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጦርነቱን ለማካሄድ ለአማልክቶቻችሁ ራሳችሁን አቅርቡ

የሚያጠቃው ጦር ሰራዊት ለአማልክቶቻቸው የአምልኮ ስርዓት በመፈጸምና መስዋዕት በማቅረብ አማልክቶቻቸው በጦርነቱ ጊዜ እንዲረዷቸው ማረጋገጫ ለመስጠት እየሞከሩ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳችሁን በማንጻትና ለአማልክቶቻችሁ መስዋዕት በማቅረብ ለጦርነቱ ተዘጋጁ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ተነሱ፣ እናጥቃቸው

መነሳት ወይም መቆም መመልከትንና ማሰብን በማቆም ይልቁንም እርምጃ መውሰድ መጀመርን የሚያሳይ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማሰብ እናቁምና ለማጥቃት እንጀምር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀትር እናጥቃ

“ኢየሩሳሌምን በቀትር እናጥቃት”

ቀኑ እየመሸ መሆኑ በጣም መጥፎ ነው፣ የማታውም ጥላ ረዝሟል

ምንም እንኳ ቀኑ እየጨለመ ቢመጣም ጦር ሰራዊታቸው መዋጋቱን እንዲቀጥል በሚፈልጉበት ጊዜ ነገስታቱ በቀኑ መጨረሻ ይህን ንግግር ይናገራሉ”

ቀኑ እየመሸ ነው

የቀኑ የመጨረሻው ብርሃን እየጨለመ ከመምጣቱ ጋር ተነጻጽሮ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቀኑ እያለቀ ነው” ዌም “መጨለም ጀምሯል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ረዝሟል

“በጣም እየተለወጠ ነው” ወይም “በጣም እየረዘመ ነው”

በሌሊት

“ቢጨልምም በሌሊት ወቅት”

የእርሷ ምሽጎች

ሰዎች ብዙ ጊዜ ስለ ከተሞች ሲናገሩ ሴቶች እንደሆኑ አድርገው ይናገራሉ፡፡ እዚህ ላይ “የእርሷ” የሚለው ኢየሩሳሌምን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኢየሩሳሌም ጠንካራ ሕንጻዎች” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)