am_tn/jer/06/01.md

5.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር እየተናገረ ነው፡፡

ከኢየሩሳሌም በመሸሽ … ደህንነትን አግኙ

እዚህ ላይ “ደህንነትን አግኙ” የሚለው ለመዳን እንዲችሉ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኢየሩሳሌምን ለቅቆ በመውጣት … ከአደጋ ዳኑ” ወይም “ከአደጋ መዳን እንድትችሉ … ከኢየሩሳሌም ለቅቃችሁ ውጡ” ( ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የቢኒያም ሕዝብ

እግዚአብሔር የሚናረው ለእነዚህ ነው፡፡

በቴቁሔ መለከት ንፉ

መለከት ሰዎች ጥቃት እንደሚደርስባቸው ለማስጠንቀቅ የሚነፋ መሳርያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጥቃት እንደሚደርስባቸው ለሕዝቡ ለማስጠንቀቅ በቴቁሔ መለከትን ንፉ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ቴቁሔ

ይህ ከደቡባዊ ኢየሩሳሌም 18 ኪሎ ሜትር ያህል የሚርቅ የከተማ ስም ነው፡፡ የከተማው ስም ትርጉም “የሚነፋ መለከት” ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ምልክቱ ከእሳት የሚወጣ ጢስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላት እየመጣ እንደሆነ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ ጢስ ወደ ላይ እንዲወጣ ለማድረግ በቤትሐካሪም እሳት አንድዱ” ወይም “ 2) ምልክቱ ሰንደቅ ዓላማ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላት እየመጣ እንደሆነ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ በቤትሐካሪም ከተማ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጉ”

ቤትሐካሪም

ይህ ከደቡባዊ ኢየሩሳሌም 10 ኪሎ ሜትር ያህል የሚርቅ የከተማ ስም ነው፡፡ የከተማው ስም ትርጉም “የወይን አትክልት ቦታ” ማለት ነው፡፡

ክፋት ከሰሜን ይመጣል

እዚህ ላይ “ክፋት” የሚለው ጥፋትና ጥፋቱን የሚያመጡትን ሰዎች የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች ከሰሜን ይመጡና በእናንተ ላይ ጥፋት እንዲመጣ ያደርጋሉ” ወይም “ከሰሜን የሚመጡ ጠላቶች ያጠፉአችኋል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ ጥፋት ይመጣል

ጥፋቱ እንዴት እንደሚመጣ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች ይመጡና ያጠፉአችኋል” ወይም “ጠላቶች ይመጡና ያፈርሷችኋል” “(ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የጽዮን ሴት ልጅ፣ ውብና ሽሙንሙን

ጽዮን ለኢየሩሳሌም ሌላኛው ስም ነው፡፡ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ሲናገር ሴት እንደሆነች አድርጎ ይገልጻታል፡፡ እርሱ ለኢየሩሳሌም ያለውን ፍቅር ለማሳየት እንደ ሴት ልጅ አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ውድ ጽዮን፣ እንደ ውድና ሽሙንሙን ሴት የመሰልሽ” ወይም “የእኔ ውድ ጽዮን” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እረኞችና በጎቻቸው ወደ እነርሱ ይሄዳሉ

ብዙ ጊዜ ነገስታት የሕዝባቸው እረኞች እንደሆኑ ተደርጎ ይነገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገስታቱና ወታደሮቻቸው ወደ እነርሱ ይሄዳሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሷ ላይ በዙርያዋ በሙሉ ድንኳኖቻቸውን ይተክላሉ

“በእርሷ ላይ” የሚለው ቃል “ጽዮንን ለማጥቃት” ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሷን ለማጥቃት እነርሱ በጽዮን ዙርያ በሙሉ ድንኳኖችን ይተክላል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እያንዳንዱ መንጋውን ያሰማራል

እግዚአብሔር ነገስታቱ ምድሪቱን ለማጥፋት ጦር ሰራዊቶቻቸውን ስለመምራታቸው ሲናገር ሳር እንዲግጡ መንጎቻቸውን እንሚያሰማሩ እረኞች አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ንጉስ እንደ እረኛ ጦር ሰራዊቱን ይመራል” ወይም “እያንዳንዱ ንጉስ ጦር ሰራዊቱን ይመራል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በራሱ እጅ

እዚህ ላይ “እጅ” የሚለው አንድ ሰው በእጁ እንዲወስደው የተመደበለት የአንድ ነገር ድርሻ ይወክላል፡፡ እዚህ ላይ ንጉስ አሸንፎ እንዲይዘው የተመደበለት የመሬት ድርሻ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የመሬት ድርሻውን አሸንፎ ይይዛል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)