am_tn/jer/04/30.md

3.7 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡-

እግዚአብሔር ለይሁዳ ሕዝብ ሴተኛ አዳሪ እንደነበሩ አድርጎ ይናገራቸዋል ምክንያቱም እነርሱ ሌሎች አማልክትን በማምለክ ለእርሱ ታማኞች ስላልነበሩ ነው፡፡

አንቺ ለጥፋት የተዳረግሽ ሆይ፣ አሁን ምን ትሰሪያለሽ?

ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ራሳቸውን ለመርዳት ሊያደርጉት የሚችሉት ምንም ነገር እንደሌለ ለእስራኤል ሕዝብ ለመንገር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አሁን ጠላቶቻችሁ ለጥፋት ዳርገዋችኋል፣ እርዳታ ለማግኘት ልታደርጉ የምትችሉት ምንም ነገር የለም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ቀይ ለበስሽ … በወርቅ አጌጥሽ … ዓይኖችሽን … በኵል ተኳልሽ

እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሲናር ወንዶችን ወደራሷ ለመማረክ ራስዋን እንደምታስውብ ሴተኛ አዳሪ እንደነደበሩ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ሴተኛ አዳሪ ቀይ ለበስሽ … በወርቅ አጌጥሽ … ዓይኖችሽን … በኵል ተኳልሽ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀይ ልብስ ለበስሽ

እዚህ ላይ “ቀይ” የሚለው ውድ የሆነ ቀይ ልብስን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውድ የሆነ ቀይ ልብስ ለበስሽ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ራስሽን በወርቅ ጌጣጌጥ አጌጥሽ

“የወርቅ ጌጣጌጥ አደረግሽ”

የተወዳጀሻቸው ወንዶች አሁን ትተውሻል

እግዚአብሔር ይሁዳ ለባለጠግነትና ለንግድ ስለተማመነችባቸው መንግስታት ሲናገር ይሁዳን እንደተወዳጁ ወንዶች አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ እነዚህ መንግስታት የእግዚአብሔርን ፍርድ ሲመለከቱ ይሁዳን ይተዉአታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ሕይወትሽን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው

እዚህ ላይ “ሕይወትሽን ለማጥፋት እየሞከሩ ነው” የሚለው የይሁዳን ሕዝብ ለመግደል እየሞከሩ መሆናቸውን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ አንቺን ለመግደል እየሞከሩ ነው” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በወሊድ እንደምትጨነቅ

ይህ ተነጻጻሪ ዘይቤ ጥቅም ላይ የዋለው ይሁዳ ምን ያህል ክፉኛ እንደምትጨነቅ ለማሳየት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሴት ልጅ በምትወልድበት ጊዜ የሚሰማት ዓይነት ሕመምና ስቃይ ከባድ ጭንቀት” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጽዮን ሴት ልጅ

እግዚአብሔር ስለ እነርሱ እንደ ሴት ልጁ አድርጎ በመናገር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ፍቅሩን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውድ ሴት ልጄ፣ ጽዮን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወዮልኝ

“እኔ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነኝ”

ተዝለፈለፍሁ

“እኔ እየደከምሁ ነው”