am_tn/jer/04/27.md

2.0 KiB

ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች

“የይሁዳ ምድር ሁሉ ባድማ ትሆናለች” ወይም “የይሁዳ ምድር ሁሉ ትፈራርሳለች”

ምድሪቱ ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጨልማል

ምድሪቱ ራሷ ታላቅ ሃዘን እየገለጸች ነው ብሎ በመናገር ኤርምያስ የእግዚአብሔርን ፍርድ አጽንዖት ይሰጣል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ኋላ አልልም

“ሃሳቤን አልለውጥም”

እነዚህን ከማድረግ አልመለስም

እዚህ ላይ “አልመለስም” የሚለው እሰራለሁ ብሎ የተናገረውን ነገር ላለመስራት መወሰኑን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እሰራለሁ ብየ የተናገርሁትን ነገር ስለመስራቴ ሀሳቤን አልለውጥም” ወይም “እኔ ለመስራት ያቀድሁትን ነገር መስራቴን አልተውም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከተማ ሁሉ

እዚህ ላይ “ከተማ” የሚለው በከተማ የሚኖረውን ሕዝብ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የከተማው ሁሉ ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ፈረሰኞች

ፈረሶች የሚጋልቡ የወታደሮች በቡድን

ወደ ችፍግ ደን ይገባሉ

ለደህንነታቸው ሲሉ ወደ ችፍግ ጫካዎች ይሮጣሉ፡፡

ከተሞች ሁሉ ባዶ ቀርተዋል፣ የሚኖርባቸው አንድም ሰው የለም

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡:፡ ሁለተኛው ሀረግ በመጀመርያው ሀረግ ውስጥ ያለውን ሃሳብ ያጠናክረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተሞች ሰው አልባ ይሆናሉ፡፡ በእነርሱ ለመኖር የቀረ አንድም ሰው የለም፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)