am_tn/jer/04/23.md

1.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡-

ኤርምያስ በኋላ ስለሚሆኑት ነገሮች እግዚአብሔር የሰጠውን ራዕይ ያብራራል፡፡

እነሆ

እዚህ ላይ “እነሆ” የሚለው ቃል ተከታዩን አስደናቂ መረጃ ልብ እንድንል ያነቃናል፡፡

ቅርጽ የለሽና ባዶ

ራእዩ ሕዝቡ በሙሉ ምርኮኛ ሆነው ከተወሰዱ በኋላ የእስራኤል ምድር ምን እንደምትመስል የሚያሳይ ትንቢት ነው፡፡

ለሰማያት ብርሃን አልነበራቸውም

“በሰማይ ላይ ብርሃን አልነበረም”

ከተሞች በሙሉ ፈራርሰዋል

“ከተሞች በሙሉ ጠፍተዋል” ወይም “ከተሞች በሙሉ የፍርስራሽ ክምር ሆነዋል”

በእግዚአብሔር ፊት፣ በእርሱ ብርቱ ቁጣ ፊት

ይህ እነዚህ ነገሮች በሙሉ የተፈጸሙት እግዚአብሔር በይሁዳ ሕዝብ ላይ በመቆጣቱ ምክንያት እንደሆነ ያመለክታል፡፡