am_tn/jer/04/21.md

1.7 KiB

እስከ መቼ የጦርነት ዓርማ እመለከታለሁ? እስከ መቼስ የመለከቱን ድምፅ እሰማለሁ?

ኤርምያስ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ለዚህ ያህል ረጅም ጊዜ የጦርነት ዓርማ ስለመመልከቱና የመለከቱን ድምፅ ስለመስማቱ ያለውን ጭንቀት ለማሳየት ነው፡፡ ጦርነቱ በፍጥነት ቢያልቅ ይመኛል፡፡ ይህ በግነት መልክ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጦርነቱ ቢያልቅና የጦርነት ዓርማው ቢወርድ እና የጦር ሰራዊቱ የመለከት ድምጽ ቢቆም እንዴት እመኝ ነበር” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጦርነት ዓርማ

“የጦጦነት ሰንደቅ ዓላማ”

የመለከት ድምፅ

አንድ ሰው ለጦርነት ጥሪ ለማድረግ እንደ ምልክት መለከት ይነፋል፡፡

ሕዝቤ ሰንፈዋልና … በጎ ነገርን ማድረግ አያውቁም

እግዚአብሔር እንዲህ እንደተናገረ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ምናልባት እግዚአብሔር ጦርነቱ አሁንም ለምን እየተካሄደ እንደሆነ ለኤርምያስ የሰጠው ምላሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፣ ‘በሕዝቤ ሞኝነት ምክንያት ነው … በጎ ነገርን ማድረግ አያውቁም፡፡’” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝ ሕዝብ

“ደደብ ሕዝብ”