am_tn/jer/04/19.md

1.7 KiB

ልቤ! ልቤ!

እዚህ ላይ “ልብ” እንደ ሀዘንና ፍርሃት የመሳሰሉ የሚያሰቃዩ ስሜቶች ይወክላል፡፡ ሀረጎቹ የተደጋገሙት የስቃዩ ጥልቀትን ለመግለጽ ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ በልቤ ጭንቀት አለብኝ

ተናጋሪው ከባድ አካላዊ ሕመም የሚያመጣ ከባድ ስሜታዊ ሕመም ተሰምቶታል፡፡

በውስጤ ልቤ ታውኮብኛል

“በውስጤ ልቤ ከመጠን በላይ ይመታል፡፡” እዚህ ላይ “ልብ” የሰውነት ክፍልን ያመለክታል፡፡ ልቤ የሚታወከው ከመደበኛው በላይ በጣም ጠንካራና ፈጣን በሆነ መልኩ ስለሚመታ ነው፡፡

ሁከት

ግራ መጋባት፣ አመጽ፣ ወይም ምስቅልቅል የሆነ ነገር የተሞላበት፤ ያልተረጋጋ ወይም ያልሰከነ

በድንገትም ድንኳኔ ጠፉ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች በድንገት ድንኳኔን አፈረሱት” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በቅጽበት ዓይን መጋረጃዎቼ ጠፉ

“ጠፉ” የሚለው ቃል ከበፊቱ ሀረግ በሚገባ መረዳት ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መጋረጃዎቼ በቅጽበት ዓይን ጠፉ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)

መጋረጃዎች

መጋረጃዎች በድንኳን ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ለመከፋፈል የሚሰቀሉ ጨርቆች ናቸው፡፡