am_tn/jer/04/16.md

3.2 KiB

ጠባቂዎች ይመጣሉ

“ጠባቂዎች” በከተማው የሚኖሩ ሰዎች የምግብና የውኃ አቅርቦት እንዳያገኙ ለመጠበቅ ከተማይቱን የሚከብቡ ወታደሮች ናቸው፡፡

እነርሱ በዙሪያዋ ከብበው እንደ እርሻ ጠባቂዎች ይሆኑባታል

ሰዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡና ወደ ውጭ እንዳይወጡ ከተማን በጥንቃቄ መጠበቅ ሰዎች ከእርሻ እንዳይሰርቁ እርሻን በጥንቃቄ እንደሚጠብቁ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተመቻቸ እርሻን በጥንቃቄ እንደሚጠብቁ ጠባቂዎኢየሩሳሌምን በጥንቃቄ ይጠብቁአታል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷን ዙርያዋን ሁሉ ከብበው

“እርሷ” የሚለው ቃል ኤሩሳሌምን ያመለክታል፡፡ ኢየሩሳሌም ብዙ ጊዜ እንደ ሴት እንደሆነች ተደርጋ ትነገራለች፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሷ በእኔ ላይ ዓመፀኛ ነበረች

“እርሷ” የሚለው ቃል ኢየሩሳሌምን ያመለክታል፣ የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ደግሞ ይወክላል፡፡ “እኔ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኢየሩሳሌም ሕዝብ በእኔ ላይ አመፀኞች ነበሩ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የገዛ ጠባይሽና ሥራሽ እነዚህን ነገሮች አድርጎብሻል

እዚህ ላይ “ጠባይ” እና “ስራ” ነገሮችን ማድረግ የሚችሉ ሰዎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አነዚህ ረቂቅ ስሞች “የሰራችሁት ስራ” በሚለው ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህ ነገሮች በእናንተ ላይ የደረሱት በሰራችሁት ስራ ምክንያት ነው” (ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ልብሽን ይሰብራል

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ቃል ምናልባት ስሜትን ያመለክታል፣ “ልብሽን የይብራል” የሚለው ሀረግ ደግሞ ምናልባት በከፋ መልኩ እንዲሰቃዩ ማድረጉን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ልብሽን በጥልቀት እንደሚሰብር ይሆንብሻል” ወይም “በጣም አስደንጋጭ በሆነ ጭንቀት እንድትሰቃዪ ያደርግሻል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)