am_tn/jer/04/11.md

1.9 KiB

እንዲህ ተብሎ ይነገራል

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ይናራል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚያቃጥል ነፋስ በምድረ በዳ ካሉ ከወናዎች ኮረብቶች … ጽኑ የሆነ ነፋስ

እዚህ ላይ “የሚያቃጥል ነፋስ” የሚለው በጣም አጥፊና ምህረት አልባ ጠላትን ይወክላል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይመጣል

“ይጓዛል” ወይም “ይፈጥናል”

የሕዝቤ ሴት ልጅ

እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንደ ሴት ልጅ አድርጎ በመናገር ፍቅሩን ያሳያል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቤ፣ ለእኔ እንደ ሴት ልጅ የሆኑት” ወይም “ውድ ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አያበጥራቸውም ወይም አያጠራቸውም

“ማበጠር” እና “ማጥራት” የሚሉት ቃላት ጠቃሚ ያልሆነውን ሽፋን ከእህል ማራገፍን ያመለክታል፡፡ ለዚህ የሚያስፈልገው ቀላል ነፋስ ብቻ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገለባውን ከእህል ለመለየት የሚያስፈልገው ቀላል ነፋስ አይሆንም” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ and ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ትዕዛዝ ይመጣል

“እኔ እንዲመጣ ባዘዝሁት ጊዜ ይመጣል”

በእኔ ትዕዛዝ

ይህ አገላላጽ በዕብራይስጡ በአንዳንድ የቅርብ ጊዜ ትርጉሞች “ለእኔ” ወይም “በእኔ” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡

ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ

“ቅጣታቸውን አውጃለሁ”