am_tn/jer/04/09.md

1.4 KiB

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል

እዚህ ላይ “ልብ” የሚለው ወኔን ይወክላል፡፡ በተጨማሪ “ልብ ይሞታል” የሚለው ወኔ ማጣትንና መፍራትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ንጉሡና መኳንንቱ ወኔአቸው ይጠፋል” ወይም “ንጉሡና መኳንንቱ ይፈራሉ” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰይፍ በሕይወታቸው ላይ ተቃጥቷል

እዚህ ላይ ሕዝቡን ለመግደል ስለተዘጋጁት ጠላቶች ሲናገር ሰይፉ በሰዎች ላይ እንደሚሰነዝር ሰው ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችን በሰይፋቸው እኛን ለማረድ ተዘጋጅተዋል” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)