am_tn/jer/04/07.md

2.3 KiB

አንበሳ እየመጣ ነው

እግዚአብሔር በጣም ኃያል ስለሆነ ጦር ሰራዊት ሲናገር በጣም ኃይለኛ ተናካሽ አንበሳ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃይለኛና ምህረት አልባ ጦር ሰራዊት እየቀረበ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጭፍቅ ዱር

ተጠጋግተው አብረው ያደጉ የቁጥቋጦ ክምችት

ሕዝብን የሚያጠፋ አንድ ሰው

እዚህ ላይ “አንድ ሰው” የሚለው ንጉስና ሰራዊቱን የሚወክል ነው፡፡ (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወጥቶአል

ይህ ፈሊጥ መንቀሳቀስ መጀመሩን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መዝመት እየጀመረ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድርሽን ባድማ የሚያደርግ

ይህ ሰዎች ምድሪቱን ሲመለከቱ ድንጋጤ የሚፈጥርባቸው ዓይነት ጥፋት የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድርሽን ለማጥፋት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ማቅ ልበሱ

ሰዎች በጣም ኃዘንተኞች እንደሆኑ ለመግለጽ ማቅ ይለብሳሉ፡፡ በዚህ ዓውድ ሕዝቡ ስለሰሩአቸው ክፉ ስራዎች በጣም ማዘናቸውን ለማሳየት ሊሆን ይችላ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማዘናችሁን የሚያሳዩ ልብሶችን ልበሱ” (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ዋይ በሉ

በከፍተኛ ጩኸት ማልቀስ

የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና

“ቁጣ” ከሰዎች ሊመለስ የሚችል ሕይወት ያለው ነገር እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ እዚህ ላይ “የእግዚአብሔር ቍጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰም” የሚለው እግዚአብሔር አሁንም በሕዝቡ ላይ ተቆጥቷል ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር አሁንም በሕዝቡ ላይ በጣም ተቆጥቷልና” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)