am_tn/jer/04/04.md

3.3 KiB

ለእግዚአብሔር ራሳችሁን ግረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ

እግዚአብሔር ሕዝቡ ለእርሱ ያለውን ታማኝነት በአካል በሚገለጥ የቃል ኪዳን ምልክት መግለጫ ቋንቋ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አቅርቡ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ራሳችሁን ግረዙ … የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታወነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለተቱም አንድ ላይ ትዕዛዙን አጽንዖት ይሰጡታል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል

እግዚአብሔር ከመጠን በላይ ስለመቆጣቱ ሲናገር ቁጣው እሳት እንደሆነ አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቍጣዬ እንደ እሳት ይነድዳል ማንም ሊያጠፋው አይችልም” ወይም “እኔ ከመጠን በላይ እቆጣለሁ እኔን ማቆም የሚችል ማንም የለም” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣ

“ታላቅ ንዴት”

በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለቱም በአንድ ላይ ትዕዘዙን አጽንዖት ይሰጡታል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነትየሚለውን ይመልከቱ)

በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች እንዲሰሙት አድርጉ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ

መለከት ሰዎችን ጠላቶቻቸው ሊያጠቁአቸው እየመጡ እንደሆነ ያስጠነቅቃል፡፡

ወደ ተመሸጉት ከተሞች እንሂድ

እነርሱ ከጠላቶቻቸው ለመዳን ወደ ተመሸጉት ከተሞች ይሄዳሉ፡፡

ክፉ ነገር … ታላቅ ጥፋት

እነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ “ታላቅ ጥፋት” የሚለው ሀረግ “ክፉው ነገር” ምን እንደሚሆን ያብራራዋል፡፡ (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና

ይህ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን ለማምጣት ከሰሜን ጦር ሰራዊት እንደሚልክ የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እናንተን እንዲያጠፋ ከሰሜን ጦር ሰራዊት እንዲመጣ አደርጋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሰሜን

ይህ ከሰሜን የሚመጣውን የጠላት ጦር ሰራዊት የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)