am_tn/jer/04/01.md

4.7 KiB

እስራኤል ሆይ፣ ብትመለስ

እዚህ ላይ “መመለስ” የሚያመልኩትን ለመለወጥ ተለዋጭ ዜቤ ነው፣ እስራኤል ደግሞ የእስራኤልን ሕዝም የሚወክል ምትክ ስም ነው፡፡ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጣዖቶችን ያመልክ ነበር፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የምትመለስ ከሆነ” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ የምታመልከውን የምትለውጥ ከሆነ” ( ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

በመመለስህ ለእኔ ትሆናለህ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ ወደ ማን መመለስ እንዳለባቸው አጽንዖት የሚሰጥ ትዕዛዝ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ እኔ ተመለስ” ወይም “እኔን አምልክ” 2) ይህ ሁኔታዎችን የሚያብራራው የመጀመርያው ሀረግ ድጋሚ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ እኔ የምትመለስ ከሆነ” ወይም “እንደገና እኔን ማምለክ የምትጀምር ከሆነ” (ምትክ ስም እና ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አስጸያፊ ነገሮችህን ከፊቴ ብታስወግድ

እዚህ ላይ “አስጸያፊ ነገሮች” የሚለው እግዚአብሔር የሚጠላቸው ጣዖቶችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አስጸያፊ ጣዖቶችህን ከእኔ ፊት ብታስወግድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከእኔ ርቀህ መቅበዝበዝ ብትተው

እዚህ ላይ “መቅበዝበዝ” የሚለው ታማኝ ላለመሆን ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእኔ ታማኝ ሆነህ ብትቀጥል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሕያው እግዚአብሔር

“እግዚአብሔር በእርግጠኝነት ሕያው እንደሆነ ሁሉ፡፡” ሕዝቡ ይህን መግለጫ የሚጠቀሙት ቀጥለው የሚናገሩት ነገር በእርግጠኝነት እውነት እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ የማይናወጥ ቃል ኪዳን የማድረግ መንገድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በማይናወጥ መልኩ እምላለሁ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ

እዚህ ላይ “አሕዛብ” ለሌሎች መንግስታት ሕዝቦች ምትክ ስም ነው፡፡ “እርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ የሚናገረው እግዚአብሔር ስለሆነ “እኔ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሌሎች መንግስታት ሕዝቦች በእኔ ይባረካሉ” (ምትክ ስም እና አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

አሕዛብ በእርሱ ይባረካሉ

እዚህ ላይ “በእርሱ ይባረካሉ” የሚለው እንዲባርካቸው እግዚአብሔርን ለመጠየቃቸው ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሌሎች መንግስታት ሕዝቦች እንዲባርካቸው ይጠይቁታል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ይከበራሉ

“እርሱ” የሚለው ቃል እግዚአብሔርን ያመለክታል፡፡ የሚናገረው እግዚአብሔር ስለሆነ “እርሱ” የሚለው “እኔ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእኔ ይመካሉ” ወይም “እኔን ያመሰግኑኛል” (አንደኛ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ዕዳሪውን መሬታችሁን እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ

እግዚአብሔር ዘር ለመዝራት መሬቱን እንደሚያዘጋጅ ገበሬ አእንደዚሁ ሕይወታቸውን እንዲያዘጋጁ ለሕዝቡ ይነግራቸዋል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)