am_tn/jer/02/29.md

4.3 KiB

ታዲያ ለምን እኔን ክፋት እንዳደረግሁባችሁ ትከስሱኛላችሁ? በእኔ ላይ ኃጢአት ያደረጋችሁ እናንተ ሁላችሁ ናችሁ፡፡

እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው የእስራኤል ሕዝብ ክፉ እንዳደረገባቸው በማሰብ እርሱን መውቀሳቸውን ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤል፣ ምንም እንኳ በእኔ ላይ ኃጢአት ማድረግን ብትቀጥሉም፣ እኔን በጠራችሁ ጊዜ ሳላድናችሁ በመቅረቴ እኔ ትክክል እንዳልሆንሁ አሰባችሁ” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ተግሣጽን አልተቀበሉም

እዚህ ላይ “ተግሳጽ መቀበል” ከቅጣት መማርን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተግሳጽ መማርን አልተቀበሉም” ወይም “እኔ እነርሱን በገሰጽሁ ጊዜ እኔን መታዘዝን ለመማር ፈቃደኞች አልሆኑም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰይፋችሁ እንደሚያጠፋ አንበሳ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል

እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ ነቢያቶቻቸውን ስለመግደላቸው ሲናገር ሰይፋቸው ነቢያቶቻቸውን የበላ አንበሳ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ነቢያቶቻችሁን እንደሚያጠፋ አንበሳ በጭካኔ በሰይፋችሁ ገደላችኋቸው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አጥፊ

መጠኑ በጣም ሰፊ የሆነ አደጋ የማምጣት ችሎታ ያለው

የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ! ቃሌን አስተውሉ፣ የእግዚአብሔር ቃል

“ይህ ትውልድ” የሚለው ሀረግ ኤርምያስ ይኖር በነበረበት ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎችን የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ዛሬ የምትኖሩ ሰዎች፣ እኔ እግዚአብሔር ለእናንተ የምናገረውን ቃል አስተውሉ”

በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁባትን?

እዚህ ላይ “ምድረ በዳ” እና “ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር” ለአደጋ ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ አደገኛ እንደሆነ በማሰባቸው እስራኤልን ለመውቀስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለእናንተ እንደ ምድረ በዳ ወይም ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር እንደሆንሁባችሁ አሰባችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ እና መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )

ሕዝቤስ ስለ ምን “እኛ ተንከራትተናል ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል”?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ ይህን በመናገሩ ሊገስጸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ ሕዝቤ ‘መሄድ ወደምንፈልገው መሄድ እንችላለን፣ ከእንግዲህ ወዲህ እግዚአብሔርን አናመልክም’ ብላችኋል፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

መንከራተት

ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ወይም ስፍራዎች ያለ ምንም ግልጽ ዓላማ ወይም አቅጣጫ መንቀሳቀስ