am_tn/jer/02/23.md

4.5 KiB

በአሊምንም አልተከተልሁም እንዴት ትያለሽ?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በአሊምን አላመለክሁም ብሎ ለተናገረው ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “You lie when you say, ‘በአሊምንም አልተከተልሁም’ ብለሽ መናገርሽ ዋሽተሻል” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

መከተል

ይህ ለማገልገልና ለማምለክ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንቺ እዚህና እዚያ የምትሮጥ ፈጣን ሴት ግመል ነሽ

እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው ሲናገር ወንድ ግመል ለመፈለግና ከእርሱ ጋር ወሲብ ለማድረግ በሌላ አቅጣጫ እንደምትሮጥ ሴት ግመል አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ ወንድ ግመል ለመፈለግና ከእርሱ ጋር ወሲብ ለማድረግ ወደፊትና ወደኋላ እንደምትሮጥ ፈጣን ሴት ግመል ነሽ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፈጣን

በፍጥነት መሮጥ የምትችል

በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ

እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ስለማምለካቸው ሲናገር ወንድ የሜዳ አህዮች ለመፈለግ እንደምትሮጥ ሴት የሜዳ አህያ አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንቺ በምድረ በዳ እንደምትኖር ወጣት ሴት የሜዳ አህያ ነሽ፡፡ ወሲብ መፈጸም ስትፈልግ ከቁጥጥር ውጭ ትሆናለች፣ ወንድ የሜዳ አህያ ለመፈለግ ነፋስን ታሸትታለች” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምኞትዋ

ይህ ሀረግ ፈሊጥ ሲሆን የሚያመለክተው ሴት የሜዳ አህያ ከወንድ የሜዳ አህዮች ጋር ወሲብ ለመፈጸም የምትፈልግበትን ጊዜ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወሲብ ለመፈጸም ስትፈልግ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው?

ይህ ጥያቄ ጥቅም ላይ የዋለው ሴት የሜዳ አህያ ከወንድ የሜዳ አህያ ጋር ወሲብ ለመፈጸም ስትፈልግ ሊቆጣጠራት የሚችል ማንም እንደሌለ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወሲብ መፈጸም ስትፈልግ ማንም ወደኋላ ሊመልሳት አይችልም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እግርሽን ባዶ ከመሆን ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ!

እግዚአብሔር እስራኤል ሌሎች አማልክትን ለማምለክ ስለመፈለጋቸው ሲናገር እነዚህን አማልክት ለመፈለግ በምድረ በዳ ይሮጡ እንደነበር አድርጎ ገልጿቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ሐሰተኛ አማልክት ለመፈለግ እዚህና እዚያ መሮጥሽን እንድታቆሚ ነግሬሻለሁ፣ ምክንያቱም ይህ ሁሉ ድርጊትሽ ውጤቱ ጫማሽ እንዲያልቅና በጣም እንድትጠሚ የሚያደርግ ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተስፋ የለውም

“ራሳችንን በመከልከል ምንም ዓይነት ተስፋ የለም፡፡” ይህ ሌሎች አማልክትን ከመከተል ራሳቸውን ማስቆም እንደማይችሉ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ራሳችንን ፈጽሞ ማስቆም አንችልም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም

እዚህ ላይ “እንግዶች” የሚለው ባዕዳን አማልክትን የሚወክል ነው፣ እና “እከተላቸዋለሁ” የሚለው እነርሱን ማምለክ የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባዕዳን አማልክትን መከተልና እነርሱን ማምለክ አለብን!” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)