am_tn/jer/02/20.md

4.2 KiB

ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ አንቺም። አንቺ ግን “አላገለግልም አልሽ”

እዚህ ላይ “ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ” እና “እስራትሽንም ቆርጫለሁ” ከባርነት አርነት እንዳወጣቸው የሚገልጹ ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ የእስራኤል ሕዝብ በግብጽ ምድር ባሮች ነበሩ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከረጅም ጊዜ በፊት እኔ ከባርነት ነፃ አወጣኋችሁ፣ ነገር ግን አሁንም እኔን ለማምለክ እንቢ አላችሁ!” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እስራት

አንድን ሰው ወይም እንስሳ ለማሰር የሚጠቅም ሰንሰለት

ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ እና ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ

ለምን እንደተጋደሙ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ እዚህ ላይ “ማመንዘር” ለእግዚአብሔር ታማኝ ያልሆነ ሰውን የሚወክል ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች አመንዝራ ሚስት አንቺም ከእኔ ይልቅ ለጣዖቶች በመስገድ እነርሱን አመለክሽ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በታች

ከስር

እኔ እንደ ተመረጠች ወይን፣ ፍጹምም ንጹሕ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር

እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር ሕዝቡን እርሱ እንደተከለው እንደ ተመረጠ ወይን በከነዓን ታላቅ ሕዝብ አድርጎ እንደሰራው ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከሁሉ የተሻለውን የወይን ዓይነት ለመትከል እጅግ በጣም ጥሩ የሆነውን ዘር እንደሚጠቀም ገበሬ፣ እኔ እግዚአብሔር በመልካም አጀማመር እንድትጀምሩ አድርጌ ነበር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የተመረጠ ወይን

“በጣም ጥሩ ጥራት ያለው ወይን”

ፍጹም ንጹህ ዘር

እዚህ ላይ “ንጹህ ዘር” ጥሩ ካልሆነ ዘር ጋር ያልተዳቀለ በጣም ጥሩ ዘር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም ጥሩ ከሆነ ዘር የበቀለ”

ታዲያ አንቺ ብልሹ፣ የማይጠቅም ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ለመለወጡና እንደ ብልሹና የማይጠቅም ወይን ግንድ ለመሆኑ ሕዝቡን ለመገሰጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን አንቺ ብልሹና የማይጠቅም ወይን ግንድ ሆነሽ ተለወጥሽ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል

በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት የሌለው ነገር እንደረከሰ ተደርጎ ይነገራል፡፡ እዚህ ላይ “ረክሰሻል” የሚለው ለእስራኤል ኃጢአት የማያቋርጥ ማሳሰቢያ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጢአትሽን እንደ ርኩሰት አይቼዋለሁ” ወይም “ኃጢአትሽ እንደ ርኩሰት ነው፤ በደልሽ ጸንቶ ይኖራል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ እግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን ተመሳሳይ ሀረግ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጌታ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ ጌታ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)