am_tn/jer/02/18.md

2.6 KiB

ስለዚህ አሁን፣ የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?

እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ግብጽንና አሦርን አነርሱን እንዲረዱአቸው መጠየቃቸው ምንም ዓይነት መልካም ነገር እንደማያመጣላቸው ለሕዝቡ ለማስታወስ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወደ ግብጽ በመሄድ ከሺሖር ወንዝ ውኃ መጠጣት ወይም ወደ አሦር በመሄድ ከኤፍራጥስ ወንዝ ውኃ መጠጣት ለእናንተ ምንም አይጠቅማችሁም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )

የሺሖርን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብጽ መንገድ ለምን ሄድሽ? የኤፍራጥስን ወንዝ ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ለምን ሄድሽ?

እነዚህ የግብጽንና የአሦርን ሰራዊት እነርሱን እንዲረዱአቸው ለመጠየቃቸው ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ግብጻውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ … አሦራውያን እንዲረዱአችሁ ለምን ጠየቃችሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሺሖር

ይህ ከግብጽጋር የተያያዘ የአንድ ምንጭ ስም ነው፡፡ ምናልባት የአባይ ወንዝ ገባር ሳይሆን አይቀርም፡፡ አንዳንድ ትርጉሞች አባይ ብለው ይጠሩታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሺሖር ምንጭ” ወይም “የሺሖር ወንዝ” ወይም “የአባይ ወንዝ” (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፋትሽ ይገስጽሻል፣ ክህደትሽ ይቀጣሻል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ቅጣታቸው የክፉ ስራቸው ውጤት እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉና ከዳተኛ ስለሆንሽ እቀጣሻለሁ” (ሰውኛ ዘይቤ እና ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉና መራራ ነው

እዚህ ላይ “መራራ” የሚለው ቃል “ክፉ” የሚለውን ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እጅግ በጣም መራራ የሆነ ክፋት ነው” ወይም “እጅግ በጣም ክፉ ነው” (ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)