am_tn/jer/02/12.md

2.4 KiB

ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ! እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ

እግዚአብሔር መለስ ብሎ እዚያ ሆነው እርሱን እንደሚሰሙት አድርጎ ለሰማያት ይናገራል፡፡ እግዚአብሔር ይህን የሚናገረው እስራኤል የሰራችው ነገር እጅግ በጣም አስደንጋጭ እንደሆነ ለመግለጽ ነው፡፡ (እንቶኔ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰማያት ሆይ፥ በዚህ ተደነቁ! እጅግም ደንግጡና ተንቀጥቀጡ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) እግዚአብሔር በሰማይ ላይ ለሚገኙ ፍጡራን ይናገራል ወይም 2) እግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆኑ አድርጎ ለራሳቸው ለሰማያት ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል

እግዚአብሔር ስለ ራሱ የሕያው ውኃ ምንጭ እንደሆነ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱ ሕያው ውኃ ምንጭ የሆንሁትን እኔን ትተውኛል” ወይም “እንደ ሕያው ውኃ ምንጭ የሆንሁትን እኔን ትተውኛል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጕድጓዶች ለራሳቸው ቆፍረዋል

እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኛ አማልክት ሲናገር ሰዎች ውኃ ለማግኘት ሲሉ የቆፈሯቸው ጉድጓዶች እንደሆኑ አድርጎ ተናግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለራሳቸው እንደቆፈሯቸው ጉድጓዶች ወደ ሐሰተኛ አማልክት ሄደዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓዶች

ውኃ ለማከማቸት የሚረዱ ጥልቅ ጉድጓዶች