am_tn/jer/02/07.md

3.1 KiB

ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጢአትን አደረጋችሁ የሰጠኋችሁን ምድር ደግሞ በእኔ የተጠላ እንዲሆን አደረጋችሁት!” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሬን አረከሳችሁ

እዚህ ላይ “አረከሳችሁ” የሚወክለው ምድሪቱ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዳይኖራት ማድረግን ነው፡፡ ይህንን ያደረጉት በዚያች ምድር ሆነው ጣዖቶችን በሚያመልኩበት ጊዜ በእርሱ ላይ ኃጢአት በማድረጋቸው ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሬን ኃጢአት በማድረጋችሁ አረከሳችኋት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ

“በኃጢአታችሁ ምክንያት ርስቴን የተጠላ አደረጋችሁት” ወይም “ኃጢአት በማድረጋችሁ ርስቴን ገፊ አደረጋችሁት”

ርስቴ

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡-

  1. እግዚአብሔር ስለ ምድሩ ሲናገር እርሱ እንደወረሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ምድር” ወይም
  2. እግዚአብሔር ለእስራኤል ስለ ሰጣት ምድር ሲናገር እርሱ ለእነርሱ እንደ ርስት እንደሰጣቸው አድርጎ ይናገራል” አማራጭ ትርጉም፡- “ለእናንተ የሰጠኋችሁ ምድር” ወይም “እንደ ርስት ለእናንተ የሰጠኋችሁ ምድር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ

እግዚአብሔር ወዴት አለ?

ይህ ጥያቄ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ መፈለጋቸውን ማሳየት ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔርን መታዘዝ እንፈልጋለን!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ እኔ ግድ የላቸውም

“ለእኔ የተሰጡ አልነበሩም” ወይም “እኔን ተዉኝ”

እረኞቹ በእኔ ላይ አመጹብኝ

መሪዎቹ እን እረኞች እነርሱን የሚከተሏቸው ሕዝብ ደግሞ እንደ በጎች ተደርገው ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “መሪዎቻቸው በእኔ ላይ ኃጢአትን አደረጉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከንቱ ነገሮችን ተከትለው ሄዱ

እዚህ ላይ “ተከትለው ሄዱ” የሚወክለው መታዘዝ ወይም ማምለክ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከንቱ ነገሮችን ታዘዙ” ወይም “ከንቱ ነገሮችን አመለኩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከንቱ ነገሮች

ከንቱ ነገሮች ሰውን መርዳት የማይችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ እዚህ ላይ ጣዖቶችን ያመለክታል፡፡