am_tn/jer/02/04.md

4.8 KiB

የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ

ያዕቆብና እስራኤል ለአንድ ሰው የተሰጡ ሁለት ስሞች ነበሩ፣ ስለዚህ እነዚህ ሁለት ሀረጎች የሚያመለክቱት ለአንድ የሕዝብ ወገን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እናንተ የያዕቆብ ወገኖች ሁሉ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)

የያዕቆብ ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የያዕቆብን ወገኖች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የያዕቆብ ወገኖች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

“ቤት” የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤል አገርና ሕዝብ የሆኑትን የእስራኤልን ወገኖች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤላውያን” ወይም “የእስራኤላውያን ሕዝብ ወገኖች” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

አባቶቻችሁ እኔን ከመከተል የራቁት፥ የማይጠቅሙ ጣዖቶችን የተከተሉና ለራሳቸውም ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው?

እርሱ በሕዝቡ ላይ ምንም ዓይነት ክፋት ስላላደረገ ሕዝቡ እርሱን በመተው ጣዖቶችን መከተል አልነበረባቸውም ብሎ ለመናገር እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች ተጠቅሟል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለአባቶቻችሁ ምንም ዓይነት ክፋት አላደረግሁም፣ ስለዚህ እኔን ከመከተል ርቀው መሄድ አልነበረባቸውም፣ የማይጠቅሙ ጣዖቶችን ተከትለው መሄድ አልነበረባቸውም፡፡ ይህንን በማድረጋቸው እነርሱ ራሳቸው የማይጠቅሙ ሆኑ!” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን ከመከተል ርቀው ሄዱ

ይህ የሚወክለው እግዚአብሔርን መተውና ለእርሱ ታማኝ ለመሆን እምቢተኛ መሆንን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ እኔን ትተውኛል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይጠቅሙ ጣዖቶችን ተከትለው ሄዱ

ይ የሚወክለው ለጣዖቶች ታማኝ መሆንንና እነርሱን ማምለክ መምረጥን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የማይጠቅሙ ጣዖቶችን አመለኩ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይጠቅሙ ጣዖቶች

ሰዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ነገር ግን ምንም ዓይነት መልካም ነገር የማያመጡላቸው ጣዖቶች፡፡ ትርጉሙ ጠቃሚ የሆኑ አንዳንድ ጣዖቶች እንዳሉ ሰዎች እንዲያስቡ የሚያደርግ መሆን የለበትም፡፡

አላሉም

ይህ በክፍሉ የተገለጸውን መናገር ይኖርባቸው እንደነበር የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲህ ማለት ነበረባቸው” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር … ወዴት አለ?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ጥቅም ላይ መዋል ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያስፈልገናል፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣን እርሱ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በማይኖርበት … የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?

ይህ መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ እግዚአብሔር ለሕዝቡ አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ጥቅም ላይ መዋል ነበረበት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያስፈልገናል፡፡ በማይኖርበት … የመራን እግዚአብሔር እርሱ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ድርቅና ጥልቅ ጨለማ ያለበት ምድር

“ድርቅ ያለበት ምድር” በቂ ውኃ የሌለበት ምድር ነው፡፡ እዚሀ ላይ “ጥልቅ ጨለማ” ለአደጋ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በቂ ውኃ የሌለበት አደገኛ ምድር” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)