am_tn/jer/02/01.md

4.1 KiB

የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣ ሂድ

ይህ ፈሊጥ ጥቅም ላይ የዋለው ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በ ኤርምያስ 1:4 ላይ ተመሳሳይ ቃላት እንዴት እንደተረጎምኻቸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለኝ፡- ‘ሂድ’” ወይም “እግዚአብሔር ይህን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡- ‘ሂድ’” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር

“ሂድና በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ስፍራ ተናገር”

ስለ አንቺ አስባለሁ

“ስለ አንቺ አስታውሳለሁ”

በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን የቃል ኪዳን ታማኝነት፣ ፍቅርሽንም

“ታማኝነት፣” ወጣትነት፣” እና “ፍቅር” የሚሉት ረቂቅ ስሞች “ታማኝ” እና “ወጣት፣” በሚሉት ቅጽሎች እና “መውደድ” በሚለው ግስ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ወጣት በነበርሽ ጊዜ፣ ለቃል ኪዳናችን እንዴት ታማኝ እንደነበርሽ፣ እና እንዴት እንደወደድሽኝ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእጮኝነት ጊዜአችን

እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ስለነበረው ግንኙነት ሲገልጽ ሁለቱ ለመጋባት ተጫጭተው እንደነበር አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁለታችን እንድንጋባ በመጀርያ በተስማማንበት ጊዜ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘር ባልተዘራበት ምድር

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንም ሰው ዘር ባልዘራበት ምድር” ወይም “ምንም ዓይነት የምግብ ዘር ባልበቀለበት ምድር” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)

የመከሩ በኩራት ነበረች

እግዚአብሔር ስለ እስራኤል ሲገልጽ ለእግዚአብሔር የተበረከተች ስጦታ እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ እርሱ መከር በኩራት” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከመከሩ በኵራት የበሉት ሁሉ እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ

እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ጥቃት ስለፈጸሙት ሲናገር ለእግዚአብሔር ብቻ የተለየውን መስዋዕት እንደበሉ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእስራኤል ላይ ጥቃት የፈጸሙ በሙሉ ከመከሩ በኵራት እንደበሉ ሕዝብ በበደላቸው ተጠይቀዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ነገር በእነርሱ ላይ መጣባቸው

“በእነርሱ ላይ መጣባቸው” የሚለው ሀረግ በእነርሱ ላይ ሆነ ለሚለው ሃሳብ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ነገር በእነርሱ ላይ ሆነ” ወይም “እኔ በእነርሱ ላይ አሰቃቂ ነገር እንዲሆንባቸው አደረግሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር የተናገረው ቃል በእርግጠኝነት እንደሚፈጸም ለመግለጽ ስለ ራሱ በስሙ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ))