am_tn/jer/01/17.md

2.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እገዚአብሔር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አትፍራቸው … በፊታቸው አስፈራሃለሁ

እዚህ ላይ “አትፍራቸው” የሚለው ከመጠን በላይ መፍራትን ይወክላል፣ “አስፈራሃለሁ” የሚለው ደግሞ ኤርምያስን በጣም እንዲፈራ ማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አትፍራ … አስፈራሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

“ትኩረት ስጥ!”

በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ፣ እንደ ብረትም ዓምድ፣ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ

እንደ እነዚህ ነገሮች ጠንካራ መሆን እግዚአብሔር እንዲናገር የነገረውን ነገር ለመናገር ልበ ሙሉ መሆንና የማይለወጥ አቋም መያዝን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ፣ እንደ ብረትም ዓምድ እና እንደ ናስ ቅጥር ጠንካራ አድርጌሃለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብረት … ናስ

እነዚህ በዚያን ጊዜ እጅግ በጣም ጠንካራ በመሆናቸው የሚታወቁ ነገሮች ነበሩ፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱ ሁሉ

ይህ የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ከአንተ ጋር ይዋጋሉ

ይህ የሚያመለክተው የይሁዳ ሕዝብን ነው፡፡

ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው

እግዚአብሔር እርሱ የተናገረው ቃል እንደሚፈጸም እርግጠኝነቱን ለመግለጽ ስለ ራሱ በስሙ ተናግሯል፡፡ በ ኤርምያስ 1:8 ላይ ይህን እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)