am_tn/jer/01/15.md

2.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡-

እግዚአብሔር ከሰሜን ስለሚመጣው ክፉ ነገር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ሁሉ

ይህ ጅምላ ፍረጃ በሰሜናዊ ክፍል ያሉትን መንግስታት ነገስታትን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እያንዳንዱ ንጉስ” ወይም “የሰሜናዊው ክፍል ነገስታት በሙሉ” (ግነት/ግነታዊ ቋንቋ እና ጅምላ ፍረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በኢየሩሳሌም በር መግቢያ ዙፋኑን ያስቀምጣል

ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ይህ የሚወክለው በኢየሩሳሌም ላይ መግዛትን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም በር መግቢያ ላይ ይገዛል” ወይም 2) ይህ የሚወክለው በኢየሩሳሌም ላይ መፍረድ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኢየሩሳሌም ላይ ይፈርዳል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዙሪያዋ በቅጥርዋ ሁሉ ላይ

“በዙሪያዋ በቅጥርዋ ሁሉ ላይ” ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ የሚለው በኢየሩሳሌም ዙርያ ያለውን ቅጥርዋን ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚወክል ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ዙርያ ያለውን ቅጥር ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ ይሰጣሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ

“በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ” ዙፋናቸውን ያስቀምጣሉ የሚለው የይሁዳ ከተሞችን ሁሉ ለማፍረስ ለጦር ሰራዊቶቻቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውን የሚወክል ነው፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ

“እነርሱን እንዴት እንደምቀጣ እናገራለሁ”

ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ

“በይሁዳ ሕዝብ ላይ ፍርድን እናገራለሁ”

በእጃቸው ለሰሩአቸው ስለ ሰገዱ

ሕዝቡ ጣዖታቱን በራሳቸው እጆች ስለሰሩአቸው፣ ጣዖታቱ ሊሰገድላቸው የሚገቡ እንዳልሆኑ ሊያውቁ ይገባቸው ነበር