am_tn/jer/01/11.md

1.7 KiB

የእግዚአብሔር ቃል ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ

ይህ ፈሊጥ ከእግዚአብሔር የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በ ኤርምያስ 1:4 ላይ ተመሳሳይ ቃላት እንዴት እንደተረጎምኻቸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለ፡- ‘ምን’” ወይም “እግዚአብሔር ይህንን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡- ‘ምን’” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

የለውዝ ቅርንጫፍ አያለሁ አልሁ

እግዚአብሔር ለኤርምያስ መንፈሳዊ ራዕይ አሳየው፡፡

የለውዝ ቅርንጫፍ

የለውዝ ዛፍ የለውዝ ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ ነው፡፡ (የማይታወቁ ነገሮችን መተርጎም የሚለውን ይመልከቱ)

እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁ

ይህ የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚፈጽመው ዋስትና መስጠቱን ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ እፈጽመው ዘንድ ቃሌን አስባለሁ” ወይም “እኔ የተናገርሁትን እንደምፈጽመው ዋስትና እሰጣለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቃሌ እተጋለሁ

“ለውዝ” እና “እተጋለሁ” የሚሉት የዕብራይስጡ ቃላት በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እግዚአብሔር ቃሉን በእርግጠኝነት እንደሚፈጽም ኤርምያስ እንዲያስብ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡