am_tn/jer/01/01.md

3.8 KiB

ከካህናቱ አንዱ የሆነ የኬልቅያስ ልጅ ኤርምያስ

“ኤርምያስ፣ የኬልቅያስ ልጅ፡፡ ኤርምያስ ከካህናቱ አንዱ ነበር”

ኬልቅያስ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ዓናቶት

ይህ የከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የብንያም አገር

“ለብንያም ጎሳ የተሰጠች ምድር”

የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ

ይህ ፈሊጥ ጥቅም ላይ የዋለው እግዚአብሔር ለእርሱ መልእክት እንደሰጠው ለማወጅ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር መልእክት ለእርሱ ሰጠው” ወይም “እግዚአብሔር ለኤርምያስ ተናገረው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

ያህዌ

ይህ በብሉይ ኪዳን ራሱን ለሕዝቡ የገለጠበት የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህንን እንዴት መተርጎም እንደሚገባ ለመረዳት የትርጉም ቃል ገጽ ላይ ሄደው ይመልከቱ፡፡

በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን

እዚህ ላይ “ዘመን” የሚለው ንጉሱ የገዛበትን ጊዜ የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የአሞጽ ልጅ ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አሥራ ሦስተኛው … አሥራ አንደኛው

(ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

አሞጽ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንግስቱ

“የአሞጽ መንግስት”

እንዲህ ሲል መጣ

“የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ መጣ”

በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን

እዚህ ላይ “ዘመን” የሚለው ንጉሱ የገዛበትን ጊዜ የሚያመለክት ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ጊዜ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)

አምስተኛው ወር

ይህ በዕብራይስጥ የቀን መቁጠርያ አምስተኛው ወር ነው፡፡ ይህ በምዕራባውያን የቀን መቁጠርያ የሐምሌ የመጨረሻው ክፍልና የነሐሴ የመጀመርያው ክፍል ወቅት ነው፡፡ (የዕብራይስጥ ወራቶች እና ደረጃ የሚያሳይ ቁጥር የሚለውን ይመልከቱ)

የሴዴቅያስ

ይህ የሴዴቅያስን አመራር የሚያመለክት ነው፡፡ ይህ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሴዴቅያስ የመንግስቱ ዘመን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የኢየሩሳሌም ሕዝብ እንደ እስረኞች በተወሰዱበት ጊዜ

ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ወደ ባቢሎን እንደተወሰዱ በግልጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የባቢሎን ሰራዊት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንደ እስረኞች በወሰዳቸው ጊዜ” ወይም “የባቢሎን ሰራዊት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንደ እስረኞች ወደ ባቢሎን በወሰዳቸው ጊዜ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)