am_tn/jdg/21/06.md

1.3 KiB

ወንድማቸው ብንያም

ይህ የሚናገረው ስለ ብንያም ነገድ ሲሆን ለነገዱ ያላቸውን ቅርበት ለማሳየት እንደ እስራኤል ወንድም ታይቷል። አ.ት፡ “የተረፉት ብንያማውያን” (ዘይቤአዊ አነጋገር የሚለውን ተመልከት)

ከእስራኤል አንድ ነገድ ተቆርጧል

የብንያም ነገድ መጥፋት ከእስራኤል በቢላዋ የተቆረጠ ያህል ተነግሯል። ይህ ግነት ነው፣ ምክንያቱም 600 ሰዎች ገና ቀርተው ነበር። ይሁን እንጂ ብንያማውያን ሴቶች ተገድለው ስለ ነበር የነገዱ የወደፊት ዕጣ ፈንታው በጥያቄ ውስጥ ነበር። አ.ት፡ “አንድ ነገድ ተደምስሷል” (ዘይቤአዊ አነጋገር፣ ግነት እና ጥቅል አስተያየት የሚለውን ተመልከት)

ሴቶች ልጆቻችንን ላንድርላቸው በእግዚአብሔር ፊት መሐላ አድርገናልና ለተረፉት ለእነዚያ ሚስቶችን ማን ያመጣላቸዋል?

እስራኤላውያኑ ለተረፉት ጥቂት ብንያማውያን ሚስቶችን ለማቅረብ ፈልገዋል፣ ነገር ግን በምጽጳ ያደረጉት መሐላ ይህንን ከማድረግ አግዷቸዋል።