am_tn/jdg/19/18.md

1.4 KiB

ወደ ቤቱ የሚወስደኝ ማነው

ይህ ሐረግ የሚያመለክተው ሌሊቱን በዚያ እንዲያሳልፍ ሌላውን ሰው ወደ ቤቱ የሚጋብዝን ሰው ነው። አ.ት፡ “በቤቱ እንዳድር የጋበዘኝ” (የአነጋገር ዘይቤ የሚለውን ተመልከት)

የሚወስደኝ

እዚህ ጋ ሌዋዊው “እኔ” ይላል፣ ነገር ግን እርሱ እያመለከተ ያለው ራሱን፣ አገልጋዩንና ቁባቱን ጭምር ነው። አ.ት፡ “የሚወስደን”

በዚያ እንጀራና ወይን አለ

ወደ አድራጊ ድምፅ ቀይረው። አ.ት፡ “ብዙ እንጀራና ወይን አለን” (አድራጊ ወይም ተደራጊ ድምፅ የሚለውን ተመልከት)

ለእኔና ለሴት አገልጋይህ፣ እንዲሁም ከአገልጋይህ ጋር ላለው ለዚህ ወጣት

ሌዋዊው አክብሮቱን ለማሳየት ራሱንና ከእርሱ ጋር ያሉትን ሌሎቹንም በሦስተኛ መደብ አድርጎ ይናገራል። አ.ት፡ “እኔ፣ ቁባቴና አገልጋዬ” (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ መደብ የሚለውን ተመልከት)

የጎደለን ምንም የለም

ይህ አዎንታዊ መግለጫ ሆኖ ሊጻፍ ይችላል። አ.ት፡ “የሚያስፈልገን ሁሉ አለን”